በቱርክ ሱፐር ሊግ የተፈጠረው ክስተት ተቀባይነት የለውም-ፊፋ
የቱርክ እግር ኳስ ፌደሬሽንም "በጨዋታው ወቅት እና በኋላ የተፈጠረውን ክስተት በተመለከት ከተወካዮቻችን እና ከባለስልጣናት ጋር አየተነጋገርን ነው"ብሏል
ፕሬዝደንቱ ባለስልጣናት ፊነርባቼ ትራብዞንስፖርን 3-2 ማሸነፉን ተከትሎ ግጭት የቀሰቀሱትን አካላት ተጠያቂ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል
በቱርክ ሱፐር ሊግ የተፈጠረው ግጭት ተቀባይነት እንደሌለው የፊፋ ፕሬዝደንት ጊያኒ ኢንፋንቲኖ ተናገሩ።
ፕሬዝደንቱ በዛሬው እለት እንደተናገሩት ባለስልጣናት ፊነርባቼ ትራብዞንስፖርን 3-2 ማሸነፉን ተከትሎ ግጭት በቀሰቀሱት አካላት ላይ ተጠያቂነት ሊያሰፍኑ ይገባል ብለዋል።
እሁድ እለት በተካሄደው ጨዋታ የተሸነፈው ትራብዞንስፖር ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት በፊነርባቼ ተጨዋቾች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
ይህ ግጭት በዚህ የሊጉ ውድድር ዘመን ዳኛ በክለብ ስራ አስኪያጅ እና የውደድር ውጤት በተቃወሙ ደጋፊዎች ከተደበደበ በኋላ የተፈጠረ ድርጊት ነው።
የቱርክ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር እንደገለጸው የቱርክ ፖሊስ 12 ደጋፊዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
የፊነርባቼ ተጨዋቾች እሁድ አለት ማታ በግል አውሮፕላን ከትራብዞን እንዲበሩ መደረጋቸው ተገጿል።
ኢንፋንቲኖ በሰጡት መግለጫ "በቱርክ ሱፐር ሊግ ውድድር ፊነርባቼ ከትራብዞንስፖር ያደረጉትን ጨዋታ ተከትሎ የተፈጠረው ግጭት በፍጹም ተቀባይነት የለውም፤ በሜዳ ውስጥም ይሁን ከሜዳ ውጭ የነበረው በእኛ ስፖርት ማህበረሰብ ተቀባይነት የለውም።" ብለዋል።
"ተጨዋቾቹ ለሁላችንም ደስት የሚፈጥረውን ጨዋታ እንዲጫወቱ ደህንነታቸው ሊጠበቅ ይገባል" ያሉት ኢንፋንቲኖ የሚመለከታቸው ባለስጣናት በትራብዞን አሳዛኝ ድርጊት የፈጸሙትን ተጠያቂ እንዲደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
"የቱርክ እግር ኳስ በእረብሻ እየታወከ እንደሚገኝ እና ሁልጊዜ ውጥረሮች እንደሚስተዋሉበት" የትራብዞንስፖር አሰልጣኝ አብዱላህ አቪሲ ተናግረዋል።
"እዚህ ቦታ ለምን ውጥረት ይነግስበታል። ደስታችንን የመግለጽ መብት የለንም?፤ እነዚህን ነገሮች ማስወገድ አለብን" ብለዋል አሰልጣኙ።
የቱርክ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ባወጣው መግለጫ "በጨዋታው ወቅት እና በኋላ የተፈጠረውን ክስተት በተመለከት ከተወካዮቻችን እና ከባለስልጣናት ጋር አየተነጋገርን ነው"ብሏል።
ምርመራው ከተጨናቀቀ በኋላ በጥፋተኞች ላይ ቅጣት እንደሚጣል ፌደሬሽኑ ገልጿል።