ስፖርት
ዳኛ የደበደበው የእግርኳስ ክለብ ፕሬዝደንት በቋሚነት ታገደ
ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በሌሎች በርካታ የክለቡ አባላት ላይ የእግድ፣ የማስጠንቀቂያ እና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል
ለአንድ ሳምነት የተቋረጠው የሊግ ውድድር በሚቀጥለው ማክሰኞ ይጀምራል
በቱርክ በሜዳ ላይ ዳኛ የደበደበው የእግርኳስ ክለብ ፕሬዝደንት በቋሚነት ታገዷል።
የቱርክ እግርኳስ ፌደሬሽን(ቲኤፍኤፍ) እንገለጸው የዲሲፕሊን ቦርዱ በሀገሪቱ ከተካሄደው የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ በኋላ ዳኛ የደበደበውን የአንካርጉሱ እግርኳስ ክለብ ፕርዝደንት ፋሩክ ኮካን በቋሚነት አግዷታል።
የቲኤፍኤፍ ቦርድ በከፍተኛ ሊግ እየተሳተፈ ባለው ክለብ ላይ የ69ሺ ዶላር የገንዘብ ቅጣት እና በሜዳው የሚካሄዱ አምስት ጨዋታዎችን ያለተመልካች እንዲያካሂድ ወስኗሉ።
ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ በሌሎች በርካታ የክለቡ አባላት ላይ የእግድ፣ የማስጠንቀቂያ እና የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ክለቡ ከሪዘስፖር ጋር ያደረው ጨዋታ 1-1 አቻ ከተጠናቀቀ በኋላ ኮካ ወደ ሜዳ በመግባት ጨዋታውን የመሩትን ዳኛ ሀሊል ኡመት ሜለርን ፊታቸው ላይ በቦክስ በመምታት መሬት ጥለዋቸዋል።
ኮካ በሚቀጥለው ቀን በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ቲኤፍኤፍም ወዲያው የሊግ ውድድሮች ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል።
ለአንድ ሳምነት የተቋረጠው የሊግ ውድድር በሚቀጥለው ማክሰኞ ይጀምራል።
በድብደባ የጎዳው ሜላን ሲታከም ከነበረበት የአንካራ ሆስፒታል አገግሞ ወጥቷል።