የኮፕ29 አጀንዳ ክርክሮች ከተደረጉ በኋላ ፋይናንስ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደረሰ
ተመድ እንዳስጠናው ጥናት ከሆነ በ2030 የሙቀት መጨመርን ማስቀረት የሚቻለው በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራት ቻይናን ሳይጨምር ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ማድረግ ሲችሉ ነው
በጉባኤው ላይ ከ198 ሀገራት የተውጣጡ የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ
የኮፕ29 አጀንዳ ክርክሮች ከተደረጉ በኋላ ፋይናንስ እንዲሆን ስምምነት ላይ ተደረሰ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የአየር ንብረት ጉባኤ ወይም ኮፕ29 የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለማስወገድ መላው አለም የተውጣጡ በሽዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በተገኙበት በደቡብ ካውኳሷ ሀገር ባኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የዚህ ጉባኤ ቁልፍ አጀንዳ ክርክሮች ከተካሄዱ በኋላ የፋይናንስ ጉዳይ እንዲሆን ተወስኗል።
"የፋይናስ ኮፕ" የሚል ስያሜ የተሰጠው ጉባኤው የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ለታዳጊ ሀገራት የሚሰጠውን እርዳታ መጨመር በሚቻልበት ሁኔታ ይመክራል።
ታዳጊ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጎጂ በመሆናቸው ድጎማ ሊደረግላቸው ይገባል የሚለው ጥያቄ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በተደረጉ ጉባኤዎች ሁሉ ሲነሳ ቆይቷል።
የኮፕ28 ጉባኤ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃቢር የአረብ ኢምሬትስን ፕሬዝደንትነት ለአዘርቤጃን በይፋ ባለስተላለፉበት በትናንትናው እለት እንዳሉት የፓሪሱን የአየር ንብረት ለውጥ ግቦችን ለማሳካት ፋይናንስ ወሳኝ ነው።
በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ መሻሻሎችን ለማምጣት ፋይናንስ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ጃቢር ሁሉም የመንግስት እና የግል የፋይንስ ምንጮች እንዲለግሱ ማበረታት ይገባል ብለዋል።
ዶክተር ጃቢር አለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት አንድ የጋራ ግብ እንዲያስቀምጥ እና የአለም የሙቀት መጠን ከ1 1/2 በታች ዝቅ እንዲ እንደሚፈልጉም ገልጸዋል።
በዱባይ በተካሄደው የኮፕ28 ጉባኤ ሀገራት ታዳሽ ያልሆኑ የኃይል ምንጮች ለመቀነስ እና ታዳሽ ኃይሎች ለማብዛት ታሪካዊ የተባለውን "የኢምሬትስ ስምምነት" መድረሳቸው ይታወሳል።
ተመድ እንዳስጠናው ጥናት ከሆነ በ2030 የሙቀት መጨመርን ማስቀረት የሚቻለው በፍጥነት እያደጉ ያሉ ሀገራት ቻይናን ሳይጨምር ከ2 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በየአመቱ ኢንቨስት ማድረግ ሲችሉ ነው።
በ2009 ሀብታም ሀገራት በማደግ ላሉ ሀገራት የአየር ንብረት ፋይናንስ 100 ቢሊዮን ለመስጠት ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም ማሳካት የቻሉት ሁለት አመት ዘግይተው ነበር። ደሀ ሀገራት በየአመቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ፕሮጀክት የሚውል 1ትሪሊዮን ዶላር እንዲሰጣቸው ጥሪ እያደረጉ ነው።
በአለም ቁጥር አንድ በካይ ጋዝ የምትለቀው ቻይና እና ከፍተኛ የነዳጅ አምራች የሆነችው አረብ ኢምሬትስ እስካሁን በማደረግ ላይ ያሉ ሀገራት ተብለው ቢመደቡም ለአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ የሚያዋጡ ናቸው።
ከ198 ሀገራት የተውጣጡ የሀገራት መሪዎችን ጨምሮ ከ32ሺ በላይ እየተሳተፉበት የሚገኘው ትናንት የተጀመረው የባኩ የአየር ንብረት ጉባኤ በቀጣይ ሳምንት ይጠናቀቃል።