በአዘርቤጃን እየተካሄደ ባለው የኮፕ29 ስብሰባ ላይ የተገኙት የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ምን አሉ?
የኮፕ29 የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ በአዘርቤጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል
ዶክተር አል ጃቢር ታሪካዊ የተባለው "የዩኤኢ ስምምነት" እንዲደረስ አድርገዋል ያሏቸውን አካላት አመስግነዋል
የኮፕ29 የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ በአዘርቤጃን ዋና ከተማ ባኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በስብሰባው ላይ የተገኙት የኮፕ 28 ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን አል ጃቢር በአሁኑ ወቅት ግጭቶች እና ክፍፍሎች መኖራቸውን ጠቅሰው ሀገራቸው ትብብር እና ንግግር እንዲደረግ እንደምትፈልግ ተናግረዋል።
ዶክተር አል ጃቢር በኮፕ28 ስብሰባ ታሪካዊ የተባለው "የዩኤኢ ስምምነት" እንዲደረስ አድርገዋል ያሏቸውን የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት እና ስብሰባውን ያስፈጸሙትን ሰራተኞች አመስግነዋል።
ዶክተር ጃቢር አክለው እንደገለጹት ኮፕ29 የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ወደተግባር የሚቀየርበት ነው።
በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ መሻሻሎችን ለማምጣት ፋይናንስ ወሳኝ መሆኑን የተናገሩት ዶክተር ጃቢር ሁሉይም የመንግስት እና የግል የፋይንስ ምንጮች እንዲለግሱ ማበረታት ይገባል ብለዋል።
ዶክተር ጃቢር አለም የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት አንድ የጋራ ግብ እንዲያስቀምጥ እና የአለም የሙቀት መጠን ከ1 1/2 በታች ዝቅ እንዲ እንደሚፈልጉም ገልጸዋል።
"በዱባይ ታሪካዊ የሚባል ስምምነተ ላይ ደርሰናል። ነገርግን ታሪክ የሚፈርደን በሰራነው ተጨባጭ ሰራ ነው"ብለዋል ዶክተር ጃቢር።