የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች ለምን የፋይናንስ እጥረት ያጋጥማቸዋል?
ለዘላቂ የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልገው የፋይናንስ መጠን አብዛኛውን ካለው ሀብት የሚበልጥ መሆኑ አንደኛው ምክንያት ነው
የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች ትርፋማነታቸው አስተማማኝ ሰለማይሆን ከፍተኛ የኪሳራ ተጋላጭነት ያላቸው እና የግል ዘርፉን ያርቃሉ
የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች ለምን የፋይናንስ እጥረት ያጋጥማቸዋል?
የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮጀክቶች የፋይናንስ እጥረት ያጋጥማቸዋል።
ምክንያቶቹ በርካቶች ቢሆኑም ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው።
1) ለዘላቂ የአየር ንብረት ፕሮጀክቶች የሚያስፈልገው የፋይናንስ መጠን አብዛኛውን ካለው ሀብት የሚበልጥ መሆኑ አንደኛው ምክንያት ነው።
2) አደጋ እና የተረጋጋ አለመሆን
ብዙ ከአየር ንብረት ጋር የተያያዙ ፕሮጀክቶች ትርፋማነታቸው አስተማማኝ ሰለማይሆን ከፍተኛ የኪሳራ ተጋላጭነት ያላቸው እና የግል ዘርፉን የሚያርቁ መሆናቸው
3) የፋይናንስ አቅርቦት ማነስ
በማድግ ላይ ያሉ ሀገራት በቂ ያልሆነ መሰረተልማት እና ውስን የሆነ የፋይናንስ ገቢያ በመኖሩ ምክንያት ለአየር ንብረት የሚሆን ፈንድ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል።
4) ፖሊሲ እና የቁጥጥር ጉዳይ
ወጥ እና በቂ ያልሆኑ ፖሊሲዎች እና ቁጥጥሮች ለረጅም ጋዜ በሚደረግ ኢንቨስትመንት ላይ ስጋት በመፍጠር ኢንቨስት እንዳይደረግ እንቅፋት ይሆናሉ።
5) የቴክኖሎጂ ችግሮች
የተወሰኑ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄዎች በተለይ ታዳሽ ኃይል እና ካርበን ካፕቸር ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይፈልጋሉ። ጥናትን እና እንዲህ አይት ቴክኖሎጂዎችን ፋይናንስ ማድረግ በጣም ፈታኝ ይሆናል።
6) ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን መርዳት
የፋይናንስ እርዳታው የአየር ንብረት ለውጥ ለሚያስከትለው ችግር ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው የህብረተሰብ ክፍል መድረሱን ማረጋገጥ አስቸጋሪ ነው።
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የመንግስት፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የማህበረሰብ ትበብር ወሳኝ ነው።