በጥቃቱ ከሞቱት በተጫሪ በትንሹ 5 ወታደሮች መቁሰላቸው ተገልጿል
በግብጽ ሲናይ በረሀ ጽንፈኞች አደረሱት በተባለ የሽበር ጥቃት 5 ወታደሮች ተገደሉ።
ጽንፈኛው እስላሚክ ስቴት አደረሰው የተባለው ይህ ጥቃት በሲናህ በረሀ የግብጽ መከላከያ ሰራዊት በሚቆጣጠረው ፍተሻ ኬላ ቦታ ላይ እንደደረሰ ተገልጿል።በዚህ ጥቃት አምሰት ወታደሮች ሲሞቱ ቢያንስ ስድስት ወታደሮች ደግሞ መቁሰላቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
በጥቃቱ የቆሰሉ ሰዎችም በአካባቢው ወደሚገኝ ወታደራዊ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ዘገባው ጠቅሷል።
ግብጽ ላለፉት ዓመታት በሰሜናዊ ግብጽ ሲናይ ግዛት መነሻውን በማድረግ በሽብርተኞች የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም በትግል ላይ ስትሆን ጥቃቱ በተለይም ከፈረንጆቹ 2013 ዓመት አንስቶ እየሰፋ መጥቷል።