ፖለቲካ
ግብጽ ለፍልስጤሟ ጋዛ መልሶ ግንባታ ግማሽ ቢሊዮን ዶላር መመደቧን አስታወቀች
ግብጽ በጥቃት የተጎዱት ፍልስጤማውያን ወደ ግብጽ እንዲገቡ ጥሪ አቅርባለች
በእስራኤል የአየር ድብደባ በጋዛ ብቻ እስካሁን 213 ሰዎች ተገድለዋል
ግብጽ ሰሞኑን በእስራኤል የአየር ድብደባ የተጎዳችውን ጋዛ ከተማን መልሶ ለመገንባት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር እንደምትመድብ ገልጻለች።
የግብጽ ፕሬዘዳንት ቃል አቀባይ እንዳሉት የገንዘብ ድጋፉ “የሲሲ ድጋፍ ለጋዛ ሰርጥ” በሚል የተዘጋጀ ጋዛን መልሶ የመገንባት ስትራቴጂ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማዋን መልሶ የመገንባት ስራውም በግብጽ ስራ ተቋራጮች አማካኝነት እንደሚካሄድም ተገልጿል።
ይህ የገንዘብ ድጋፉ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ከፈረንሳይ ፕሬዘዳነት ኢማኑኤል ማክሮን እና ከጆርዳኑ ንጉስ አብደላህ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው።
ግብጽ በእስራኤል የአየር ድብደባ የተጎዱ ፍልስጤማዊያን ወደ ግብጽ እንዲገቡ እና ድጋፍ እንደሚደረግላቸው
ባቀረበችው ጥሪ መሰረት ስደተኞቹ የህክምና እና ሌሎች ድጋፎች እያገኙ መሆኑ ተገልጿል።
እስራኤል በሰነዘረችው የአየር ጥቃት በጋዛ ከተማ ብቻ 213 ሰዎች ሲገደሉ፣በእስራኤል ደግሞ 10 ሰዎች ህይወታቸውን
አጥተዋል፡፡