ከመኪናነት ወደ አውሮፕላንነት ለመቀየርም 2 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ይፈጅባታል
በራሪዋ መኪና ሙከራ ከተደረገባት በኋላ በስሎቫኪያ ትራንስፖርት ባለስልጣን የበረራ ደህንነት ማረጋገጫ ወረቀት እንደተሰጣት ታውቋል።
መኪናዋ በ8 ሺህ ጫማ ከፍታ ላይ በሰዓት 160 ኪሎ ሜትር መብረር የምትችል መሆኑም ታውቋል።
እንደ መኪና በአስፓልት ላይ የምትነዳው እና አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜም ወደ አውሮፕላንት የምትቀየረዋ መኪና የቢ.ኤ.ም ደብሊው ሞተር የተገጠመላት ሲሆን፤ ለመንቀሳቀስም መደበኛ ናፍጣ ትጠቀማች ነው የተባለው።
መኪናዋ ከአውሮፕላንነት ወደ መኪናነት እንዲሁም ከመኪናነት ወደ አውሮፕላንነት ለመለወጥ 2 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ብቻ የሚፈጅባት መሆኑም ታውቋል።
በራሪዋ መኪና የ70 ሠዓት በረራ እንዲሁም 200 ጊዜ ከመሬት ወደ ሰማይ እንድትነሳ ከተደረገ በኋላ የበረራ ደህንነት ማረጋገጫ እንደተጣት ተነግሯል
በራሪዋ መኪና ከዚህ ቀደም በስሎቫኪያዋ ኒትራ እና በራቲስላቫ ከተሞች በሚገኙ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች መካከል የ35 ደቂቃ የበረራ ሙከራ አድርጋ እንደነበረ ይታወሳል።
በራሪዋ መኪና የፈጠራ ባለቤት ፕሮፌሰር ስቴፋን ከሌይን፤ በመኪናዋ በለንደን እና በፓሪስ መካከል በረራ ለማድረግ ማሰባቸውን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት የተሰጠው የበረራ ደህንነት ማረጋገጫም መኪናዋን በስፋት ወደ ማምረት የሚያስገባ እንደሆነም አስታውቀዋል።