የአማዞን ተምዘግዛጊ ወንዞች ሚስጥር
“አየር ወለድ ወንዞች" ክልላዊና ዓለም አቀፋዊ አየር ንብረት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ
የመሬት ሳንባ በመባል የሚጠራው አማዞን፤ ከዚህም በላይ በረከት አለው
አማዞን ደን የ400 ቢሊዮን በላይ ዛፎች መኖሪያና 6.7 ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር ሽፋን አለው።
የመሬት ሳንባ በመባል የሚጠራው አማዞን፤ ከዚህም በላይ በረከት አለው።
አማዞን የአየር ንብረትን ሚዛን በማረጋጋት፣ የውሃ ዑደትን በማስተካከል፤ የዝናብ ስርጭትንና ሙቀትን በመቆጣጠር ለሰብሎች እድገት ወሳኝ ሚና አለው።
በአማዞን ደን ወንዞች ሽህዎችን ኪሎሜትር አቋርጠው ይምዘገዘጋሉ። ወንዞቹ ከውሃ ትነት ላይ የተመሰረቱ ናቸው።
እነዚህ "አየር ወለድ ወንዞች" ክልላዊና ዓለም አቀፋዊ አየር ንብረት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።
ቪዥዋል ካፒታሊስት የተባለ ድረ ገጽ እንዳለው የአማዞን ወንዞች ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ትንታ መመንጨት ይጀምራሉ።
በአማዞን ደን ዛፎች በየቀኑ 20 ቢሊዮን ቶን ውሃ ወደ ከባቢ ይለቃሉ። ይህ መጠን ሚሲሲፒ ወንዝ በ13 ወራት ከሚኖረው የውሃ መጠን የሚበልጥ ነው።
በብራዚል ስድስት በመቶ ብቻ መሬት ለመስኖ የሚሆን በመሆኑ፤ አካባቢው ለሰብል ምርት ዝናብ ላይ በእጅጉ ጥገኛ ነው።
አማዞን በየዓመቱ ቢሊዮን ቶን ካርቦንዳይ ኦክሳይድ በመምጠጥ መቀት ላይ አበርክቶ አለው።
በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስና ሙቀትን ለመቆጣጠር አማዞን ደን ጥቅሙ ትልቅ ነው።