ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ የመርከቦች አስተዋጽኦ
መርከቦች በናፍጣ ምትክ ቤንዚን መጠቀም የአየር ጥራትን ያሻሽላል፤ በሰው ጤና ላይ ጎጂ ውጤቶችንም ይቀንሳል
በ2050 ብክለትን ወደ ዜሮ ለመቀነስ የባህር ማጓጓዣ ኢንዱስትሪው ቢስማማም፤ ከከፍተኛ ብክለት በሚያደርሱ ኢንዱስትሪዎች አንዱ ነው
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ፓናል፣ የነዳጅ አጠቃቀማችን የዓለምን የሙቀት መጠን መጨመር ላይ እንደሚያስጠነቅቅ ይጠበቃል።
መርከቦች በናፍጣ ምትክ ቤንዚን መጠቀም የአየር ጥራትን ያሻሽላል፤ በሰው ጤና ላይ ጎጂ ውጤቶችንም ይቀንሳል።
ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያላቸውን እንደ ሚቴን ባሉ የቅሪተ አካላት ነዳጅ ምርጫ ላይ የሚደረገው ምርመራ እየጨመረ ነው።
ምንም እንኳን በ2050 ብክለትን ወደ ዜሮ ለመቀነስ የባህር ማጓጓዣ ኢንዱስትሪው ቢስማማም፤ ከከፍተኛ ብክለት በሚያደርሱ ኢንዱስትሪዎች እየጨመረ የመጣው የአየር ንብረት ቀውስ ለመቋቋም እርምጃዎች በቂ አይደሉም በሚሉ የባለሙያዎችን ትችት አስከትሏል።
ሚቴን የተባለው ንጥረ ነጠር ለተፈጥሮ ጋዝ ዋና አካል እና በምድር ላይ ከካርቦን ዳይኦክሳይድ በኋላ ሁለተኛ ከፍተኛ መጠን ያለው የግሪንሀውስ ጋዝ ነው።
ብሉምበርግ እንደዘገበው 30 በመቶ ለሚሆነው የምድር ሙቀት ተጠያቂም ነው።
ስለዚህ ሚቴን ለምድር እንደ መከላከያ ብርድ ልብስ ሆኖ የሚያገለግል ኃይለኛ የሙቀት አማቂ ጋዝ ነው።
ሚቴን በአንጻራዊነት በአጭር ጊዜ የሚቆይ ቢሆንም በዓለም ሙቀት መጨመር ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።
ሚቴን ምድርን በማሞቅ ከካርቦን ዳይኦክሳይድ በ28 እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፤ በ20 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ይህ ንፅፅር ወደ 80 እጥፍ ደርሷል።