ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱ ሰባት ምርጥ የዓለማችን ምግቦች
እንቁላል ከፕሮቲን ይዘቱ ባለፈ ቫይታሚን ቢ ንጥረ ነገር ጥሩ እና የእረፍት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል በሚል ተጠቅሷል
በቫይታሚን ሲ እና ፖታሺየም ንጥረ ነገሮች የበለጸገው ስኳር ድንች ጭንቀቶችን እንድንቀንስ ከሚረዱ ምግብ አይነቶች መካከል ነው
ሕይወት ብብዙ ምክንያቶች አንዴ ለጭንቀት አንዴ ለደስታ እና ለሌሎችም የሕይወት ገጽታዎች ትዳርገናለ።
ዩሮ ኒውስ የስነ ምግብ ባለሙያዎችን አነጋግሮ በዓለማችን ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱ የምግብ አይነቶችን ዝንደሚከተለው አስነብቧል።
የመጀመሪያው ጭንቀትን ለማስወገድ ይረዳል የተባለው ምግብ ጎመን እና ይህን በመጠቀም የሚሰሩ ምግቦች ናቸው።
ጥቅል ጎመን ለሰውነታችን ጠቃሚ የሖኑ ባክቴሪያዎችን ፣ ቫይታሚን እና ማዕድናትን በመያዝ ጥሩ የምግብ አይነት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በተለይም በጭንቀት ምክንያት ምግብ የመመገብ ፍላጎት ላጡ ሰዎች እንዲሁም ከሆድ እቀደ የሰውነት ክፍሎች ጋር ህመም ላለባቸው ሰዎች ጥቅል ጎመን ፍቱን መድሃኒት ነው ተብሏል፡፡ ለሆድ ህመም እና አንጀት ጤንነት ጥሩ ነው።
ሌላኛው ጭንቀትን ለማስወገድ ይረዳል የተባለው የምግብ አይነት እንቁላል ሲሆን ከፕሮቲን ይዘቱ ባለፈ ቫይታሚን ቢ የተሰኘው ንጥረ ነገር ጥሩ እና የእረፍት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል በሚል ተጠቅሷል።
በተለይም በቫይታሚን ቢ ውስጥ የሚገኘው ንጥረ ነገር የነርቭ እና አዕምሮ ህዋሳት የተሳካ ተግባቦት እንዲፈጥሩ ያግዛል ተብሏል።
የባቄላ እሸትን ከሌሎች አረናጓዴ ቅጠላቅጠሎች ጋር በመቀላቀል መስራት እና መመገብ ሌላኛው ሰዎችን ከጭንቀት ይገላግላል የተባለ የምግብ አይነት ሲሆን ይህ ምግብ የምግብ ውህደትን በማቀላጠፍ እና የአንጀት ድርቀትን በማስወገድ እንደሚጠቅም ተገልጿል።
በአሚኖ አሲድ የበለጸጉ ምግቦች የሰዎችን በሽታ የመከላከል አቅም በማሳደግ ሌላኛው ሰዎችን ከጭንቀት መከላከያ ምግብ እንደሆነ ባለሙያዎች የገለጹ ሲሆን አሳ እና ጥራጥሬዎች ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናሉ ተብሏል።
ሰሊጥ እና ከሰሊጥ ጋር ተቀላቅለው የሚሰሩ የምግብ አይነቶች በተለይም ለታዳጊዎች ልጆች መመገብ የተዝናና አእምሮ እና ስራዎችን በንቃት እንዲሰሩ በማድረግ እና በሽታ የመከላከል አቅማቸውን በማሳደግ ጥሩ የምግብ ይዘት መሆኑ ተጠቅሷል።
ስኳር ድንች ሌላኛው ሰዎችን ከጭንቀት ይታደጋል የተባለ ምግብ ሲሆን በካርቦሀይድሬት ንጥረ ነገር የበለጸገ መሆኑ ደም ግፊት እና ኮሊስትሮል ጋር በተያያዘ ጭንቀት ለሚሰማቸው ሰዎች ጥሩ ምግብ ነው ተብሏል።
በቫይታሚን ሲ እና ፖታሺየም ንጥረ ነገሮች የበለጸገው ስኳር ድንች ጭንቀቶችን እንድንቀንስ ከሚረዱ ምግብ አይነቶች መካከል ዋነኛው እንደሆነ ተገልጿል።
ሰውነታችን የካንሰር አምጪ ህዋሳትን በቀላሉ እንዲከላከል አቅም በመሆን እርጅናን ይከላለካሉ ከሚባሉ ምግቦች መካከል አንዱ የሖነው እንጀሪ ደግሞ ሌላኛው የሰዎችን ጭንቀት ይቀንሳል ተብሏል።