የመንግስታቱ ድርጅት በ2019 የአለም የሻይ ቀን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 እንዲከበር ወስኗል
ሻይ ለመጀመሪያ ጊዜ መጠጣት የጀመረው ከ5 ሺህ አመት በፊት በቻይና እንደነበር ይነገራል።
የወቅቱ የቻይና መሪ ሼን ዮንግ በሻይ ቅጠል ዛፍ ስር ውሃ ሲያፈሉ ቅጠሉ ወደ ማፍያው ገብቶ የውሃውን ቀለም እና መዓዛ መለወጡም በአፈ ታሪክ ይነሳል።
ሼን ዮንግ የወደዱት ማዕዛና ቀለምም መላው ቻይናን ብሎም በሂደት አለም አዳርሷል ተብሎ ይታመናል።
በአሁኑ ወቅት በመላው አለም በየቀኑ በአማካይ 800 ሚሊየን ኩባያ ሻይ ይጠጣል።
የመንግስታቱ ድርጅትም በ2019 የአለም የሻይ ቀን በፈረንጆቹ ግንቦት 22 ተከብሮ እንዲውል ወስኖ ከ2020 ጀምሮ እየተከበረ ነው።
ይህንኑ ቀን አስመልክተንም ለጤና የሚመከረው አረንጓዴ ሻይ በረከቶችን እንጠቁማችሁ፦