አልጀሪያ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በፈረንጆቹ 1962 ነጻ ከወጣች በኋላ ቦተፍሊካ የመጀመሪያው የአልጀሪያ የውጭ ገዳይ ሚኒስትር መሆን ችለው ነበር
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቦተፍሊካ በኢትዮጵያና በኢርትራ መካከል ተከሄደው ጦርነት መቋጫ የሆነው አልጀርስ ስምምነት እንዲፈረም ሚና ነበራቸው፡፡
በፈረንጆቹ 1999 የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት ቦተፍሊካ እጅግ ከባድ የሚባለውን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት አንዲፈቱ ሃላፊነት ተጥሎባቸው ነበር፡፡
ጦርነቱ በአልጀርስ ስምምነት ማለትም በፈረንጆቹ 2000 ቢቆምም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን እስከመጡበት ጊዜ ድረስ ሁለቱ ሀገራት “ሰለም የለም፤ጦርነት የለም” በሚል ሁኔታ ውስጥ ነበሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመጀመር ሁኔታው እንዲቀየር አድርገዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ቦተፍሊካ በ84 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ቦተፍሊካ በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2019 ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ከመልቀቃቸው በፊት ሰሜን አፍካዊቷን ሀገር አልጀሪያን ለሁለት አስርት አመታት መርተዋል፡፡
የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው የቀድሞወቅ የአልጀሪ ፕሬዝዳንት ቢተፍሊካ፣ በሀገሪቱ የተካሄደውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ነበር ከሁለት አመታት በፊት ስልጣናቸውን የለቀቁት፡፡
ለሁለት አስርት አመታት አልጀሪያን ያስተዳሩጽ ቦተፍሊካ፤የአልጀሪያ የነጻነት ጦርነት ተሳታፊ የነበሪ ሲሆን በፈረንጆቹ 2019 የህዝብ ተቃውሞ በመዝዛቱ ስልጣናቸውን ለ6ኛ ዙር የማራዘም እቅዳቸውን ሰርዘው ስልጣን ለቀዋል፡፡
ቦተፍሊካ ከፈረንጆቹ 2013 እስሚሞቱበት ጊዜ ድረስ በአደባባይ ብዙም አይታዩም ነበር፡፡
ፕሬዝዳንት ቢተፍሊካ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ፣ በሀገሪቱ የተከሰተውን የህዝብ ጥያቄ ለመመለስ በማሰብ የአልጀሪ ባለስልጣናት የሙስና ወንጀል ምርመራ ይጀምራሉ፤ በምርመራውም የቦተፍሊካን ውንድም ጨምሮ ብዙ ከፍተኛ ባለስጣናት ታስረው ነበር፡፡
አልጀሪያ ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በፈረንጆቹ 1962 ነጻ ከሆነች በኋላ ቀድሞው የአልጀሪያ ፕሬዝዳንት የመጀመሪያው የአልጀሪያ የውጭ ገዳይ ሚኒስትር መሆን ችለው ነበር፡፡
ቦተፍሊካ የተመድ ጠቅላላ ስብሰባን በፕሬዝዳንትነት በመሩበት ወቅት፤ የፍለስጤሙ መሪን ያሲር አረፋትን ንግግር እንዲያደርጉ በመጋበዝ ፣ አለምአቀፉ ማህበረሰብ ለፍልስጤም ታሪካዊ እውቅና እንዲሰጥ አድገዋል፡፡