ኔቶን በዋና ጸሃፊነት እየመሩ ያሉት ጄንስ ስቶልትንበርግ የፊታችን ሀምሌ ስልጣናቸው ያበቃል
የኔቶን ለመምራት እየተፎካከሩ ያሉ መሪዎች እነማን ናቸው?
የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ወይም ኔቶ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አውሮፓን እና አሜሪካንን ከየትኛውም ጥቃት ለመከላከል በሚል ነበር የተመሰረተው፡፡
በዓለማችን ካሉ ወታደራዊ ተቋማት መካከል በጥንካሬው ቀዳሚ ነው የሚባልለት ኔቶ በአሜሪካ የበላይነት ይመራል፡፡
31 አባል ሀገራትን ያቀፈው ኔቶ ዋና ጸሃፊ በየአምስት ዓመቱ ከአባል ሀገራቱ የተውጣጣ መሪ በምርጫ ወደ ሀላፊነት የማምጣት ስርዓት አለው፡፡
በዚህም መሰረት ላለፉት አምስት ዓመታት የኔቶ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ኖርዌጂያዊው ጄንስ ስቶልትንበርግ የፊታችን ሀምሌ ስልጣናቸውን ለተተኪያቸው ያስረክባሉ ተብሏል፡፡
የኔቶ አዲስ ዋና ጸሃፊ ለመሆንም የቀድሞ ኢስቶኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ካጃ ካላስ እና የላቲቪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስት ክሪስጃኒስ ካሪንስ ሲፎካከሩ ቆይተዋል፡፡
የኔዘርላንድ ህግ አውጪ ምክር ቤት መተማመ ኛ ድምጽ የነፈጋቸው እና ስልጣናቸውን ያጡት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩት ኔቶን ለመምራት ፍላጎት ማሳየታቸውን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ኔቶ አባል ሀገራቱን ለረጅም ጊዜ ጦርነት እንዲዘጋጁ አሳሰበ
ላለፉት 13 ዓመታት ኔዘርላንድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ማርክ ሩት ኔቶን ለመምራት መፈለጋቸው ከዚህ በፊት ለነበሩት እጩዎች ዋነኛ ስጋት ይሆናሉም ተብሏል፡፡
ማርክ ሩት በተለይም በኔቶ የበላይነት አላት ከምትባለው አሜሪካ ጋር በስልጣን ዘመናቸው ወቅት የነበራቸው መልካም ወዳጅነት ፉክክሩን በበላይነት እንዲያጠናቅቁ ሊያደርግ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡
ከሩሲያ ጋር እየተዋጋች ላለችው ዩክሬን ዋነኛ የጦር መሳሪያ እና ሌሎች ድጋፎችን የሚያደርገው ኔቶ ከሩሲያ ጋር ወደ ቀጥታ ጦርነት የመግባት ስጋት እንዳለበት የወቅቱ የቃል ኪዳኑ ዋና ጸሃፊ ጄንስ ስቶልትንበርግ ተናግረዋል፡፡