ፖለቲካ
የኔቶ መሪዎች የዩክሬን "የወደፊት እጣፋንታ የሚወሰነው በኔቶ ነው" የሚል ውሳኔ ላይ ደረሱ
የኔቶ መሪዎች በሉታኒያ ቪልኒየስ ባደረጉት ስብሰባ የዩክሬን የወደፊት እጣፋንታ የሚወሰነው በኔቶ መሆኑን ተስማምተዋል
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችው ዩክሬን ኔቶን መቀላቀል አጥብቃ የምትፈልገው ነው
የኔቶ መሪዎች በሉታኒያ ቪልኒየስ ባደረጉት ስብሰባ የዩክሬን የወደፊት እጣፋንታ የሚወሰነው በኔቶ መሆኑን ተስማምተዋል።
ነገርግን መሪዎቹ ዩክሬን ወደ ኔቶ የምትገባበትን የጊዜ ሰሌዳ ወይም ግብዣ ለዩክሬን አልሰጧትም።
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችው ዩክሬን ኔቶን መቀላቀል አጥብቃ የምትፈልገው ነው።
ኔቶ ዩክሬን ማሟላት ያለባትን የአባልነት የተግባር እቅድ (ኤምፒኤ) ትቶላታል፤ ይህም ዩክሬን የጥምረቱ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ላይ የነበረውን እንቅፋት አስወግዶላታል።
"የዩክሬን እጣፋንታ ዩክሬን ወስጥ ነው" ያለው የኔቶ መሪዎች የጋራ ውሳኔ ሀሳብ የዩክሬን የዩሮ-አትላንቲክ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን አምኖበታል።
የውሳኔ ሰነዱ እንደገለጸው ከሆነ ሁሉም የኔቶ አባላት ሲስማሙ እና ዩክሬን የሚጠበቅባትን ስታሟላ ወደ ጥምረቱ እንድትገባ ግብዣ ይቀርብላታል።
ነገርግን መሪዎቹ ዩክሬን ማሟላት ያለባትን መሰፈርት ግልጽ አላደረጉም።
ዩክሬን ጥምረቱን መቀላቀል የምትፈልገው ከሩሲያ ለገባችው የማያባራ ጦርነት እንደመፍትሄ ስለምትቆጦረውም ጭምር ነው።