ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የስዊድን ኔቶን የመቀላቀል ጥያቄ እንዲጸድቅ ለፖርላማ አቀረቡ
በስዊድን ላይ ጥያቄ ስታነሳ የቆየችው ቱርክ የፊላንድን የኔቶ መቀላቀል ጥያቄ ማጽደቋ ይታወሳል
ረቂቅ ህጉ መቼ እንደሚጸድቅ ቀን አልተቆረጠለትም
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የአቀረቡ ኔቶን የመቀላቀል ጥያቄ እንዲጸድቅ ለፖርላማ አቀረቡ።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን የስዋዴን ኔቶን የመቀላቀል ጥያቄ እንዲጸድቅ ወደ ፖርላማ መምራታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
- ቱርክ ለስዊድን የኔቶ አባልነት ድጋፍ የምሰጠው በሽብርተኝነት ላይ እርምጃ ስትወስድ ነው አለች
- ስዊድን "አሸባሪዎችን ማስጠለሏን" ካለቆመች ቱርክ የኔቶ መቀላቀል ጥያቄዋን ይሁንታ አትሰጥም-ኢርዶጋን
ስዊድን በቱርክ የሚፈለጉ ሽብርተኞችን እያኖረች ነው በሚል ጠንካራ ተቃውሞ ሲያሰሙ የነበሩት ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ባለፈው ሀምሌ ወር ረቂቅ ህጉን ወደ ለፖርላማ እንደሚያቀርቡት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
ነገርግን ፖርላማው ከተከፈተ በኋላ የቱርክ ባለስልጣናት የስዊድን የኔቶ አባልነት ከመጽደቁ በፊት ስቶኮሆልም በአሸባሪነት በተፈረጀው ኩርዲስታን ወርከርስ ፖርቲ(ፒኬኬ) ላይ ተጨባጭ እርምጃ መውሰድ አለባት ሲሉ ተናግረዋል።
ፒኬኬ በቱርክ፣ በአውሮፖ ህብረት እና በአሜሪካ ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ ተፈርጇል።
በትናንትናው እለት ስዊድን አባል እንድትሆን የሚፈቅደው ረቂቅ ህግ ተንቀሳቅሷል።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን ስዊድንን የኔቶ አባል እንድትሆን በሚያደርገው የፕሮቶኮል ሰነድ ላይ መፈረማቸውን እና ለፖርላማው መምራታቸውን የቱርክ ፕሬዝደንት ጸ/ቤት በኤክስ ጉጹ ላይ ጽፏል።
የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኡሌፍ የስዊድንን ኔቶን መቀላቀል በበጎ እንደሚቀበሉት ተናግረዋል።
"አሁን ፖርላማው ጉዳዩን ማየት ብቻ ይቀረዋል"ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ረቂቅ ህጉ መቼ እንደሚጸድቅ ቀን አልተቆረጠለትም።
ስዊድን እና ፊንላንድ የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶን ለመቀላቀል የወሰኑት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ መክፈቷን ተከትሎ ነበር።
በስዊድን ላይ ጥያቄ ስታነሳ የቆየችው ቱርክ የፊላንድን የኔቶ መቀላቀል ጥያቄ ማጽደቋ ይታወሳል።