ጉብኝቱ በቤጂንግ እና በታይፔ መካከል ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው የመጣው ነው
የታይዋን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ማ ዩንግ-ጁ በፈረንጆቹ ከ1949 አብዮት በኋላ ቻይናን የጎበኙ የመጀመሪያው የታይዋን መሪ ሆነዋል።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሰላምን ለማምጣት እና ግንኙነትን ለማሻሻል ተስፋ እንዳላቸው በመግለጽ ቻይና ገብተዋል።
የ73 ዓመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ከታይዋን ከመነሳታቸው በፊት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በጉዞው "በጣም ደስተኛ ነኝ" ብለዋል።
በቆይታቸው ከተማሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ እና በቻይና የሚገኙትን ቅድመ አያቶቻቸውን እንደሚዘክሩ ተናግረዋል።
ማ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2016 በስልጣን ነበሩ።
ጉብኝቱ በቤጂንግ እና በታይፔ መካከል ከፍተኛ ውጥረት በነገሰበት ወቅት ነው የመጣው ነው።
"የታይዋን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አነጋግራለሁ። አሁን ላለው ችግር በአቋራጭ በወጣቶች መስተጋብርን በማሻሻል ሰላም በፍጥነት ይመጣል" ብለዋል።
የታይዋን ገዥው ፓርቲ ዴሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ ጉብኝቱን ወቅሶ፤ "ተገቢ አይደለም" ሲል ተናግሯል።
ማ የቤጂንግ ደጋፊ መሆኗቸውን አጥብቀው ቢክዱም ከቻይና ጋር የጠበቀ ግንኙነትን የሚደግፈው የታይዋን ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ኩኦምሚንታንግ ከፍተኛ አባል መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።