አውሮኘላን ከተከሰከሰ ሳምንታት በኋላ አራት ልጆች በህይወት ተገኙ
ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ በአማዞን ግዛት ውስጥ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ሞተሩ በመበላሸቱ የአደጋ ጊዜ ጥሪ አሰምቶ ነበር

ፕሬዝደንት ፔትሮ በካምቦዲያ ጫካ ጠፍተው የነበሩት ልጆች መገኘት ለሀገሪቱ ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል
በካምቦዲያ የተሳፈሩበት አውሮኘላን ከተከሰከሰ ሳምንታት በኋላ አራት ልጆች በህይወት መገኘታቸው ተገልጿል።
ከካምቦዳያ ነባር ጎሳ ማህበረሰብ የሚገኙት አራት ልጆች ሲበሩበት የነበረው አውሮፕላን ጫካ ውስጥ ከተከሰከሰ አምስት ሳምንታት በኋላ በህይወት መገኘታቸውን የሀገሪቱ ኘሬዝደንት ጉስታቮ ፔትሮ ተናግረዋል።
የካሞቦዲያ ጦር ልጆቹን አውሮኘላኑ በተከሰከሰበት አቅራቢያ በካኩይታ እና ጓቬሬ ግዛት አዋሳኝ ላይ ማግኘት ችሏል።
ሰባት ሰዎችን አሳፍሮ በአማዞን ግዛት ውስጥ ሲጓዝ የነበረው አውሮፕላን ሞተሩ በመበላሸቱ የአደጋ ጊዜ ጥሪ አሰምቶ ነበር።
በአደጋው አብራሪውን ጨምሮ ሶስት ጎልማሳዎች አስከሬን በአውሮፕላኑ ውስጥ ተገኝቷል። የ13፣9 ፣4 አመት ልጆች እንዲሁም የ12 ወር ህጻን በህይወት ተርፈዋል።
ፕሬዝደንት ፔትሮ በካምቦዲያ ጫካ ጠፍተው የነበሩት ልጆች መገኘት ለሀገሪቱ ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል።
ህጻናቱ አሁን ላይ በድካም ውስጥ መሆናቸውን እና የህክምና ባለሙያዎች ሁኔታቸውን እንዲያዩ እንደሚደረግ ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል።
በአነፍናፊ ውሾች የታገዙት የነፍስ አድን ሰራተኞች ልጆቹ ሲበሉት ከነበረው አትክልት የወዳደቀ ፍራፍሬ ቀደም ሲል አግኝተው ነበር።
የካምቦዲያ ጦር እና አየር ኃይል አውሮፕላኖች በፍለጋው ተሳትፈዋል።