ዩክሬን ሩሲያ ከላከችው 54 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ 52ቱን መታ መጣሏን አስታውቃለች
ሩሲያ በኪየቭ የምስረታ በዓል ትልቁን የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት አደረሰች።
የዩክሬን ዋና ከተማ እሁድ የተመሰረተችበትን ዓመታዊ በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ ባለችበት ወቅት ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በከተማይቱ ላይ ትልቁን የሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ማድረሷ ተነግሯል።
እሁድ ኪየቭ ከ አንድ ሽህ 541 ዓመታት በፊት በይፋ የተመሰረተችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው።
ዩክሬን ሩሲያ ከላከችው 54 ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ 52ቱን መታ መጣሏን የገለጸች ሲሆን፤ ጥቃቱ ኢራን ሰራሽ 'ካሚካዚ' ሰው አልባ አውሮፕላኖች የደረሰ ከፍተኛው ነው ተብሏል።
የዩክሬን አየር ኃይል በቴሌግራም እንዳስታወቀው ሩሲያ በማዕከላዊ የሀገሪቱ ክልሎች እና በኪየቭ ወታደራዊ እና ወሳኝ የመሠረተ ልማት ተቋማትን ኢላማ አድርጋለች።
በኪየቭ ላይ ምን ያህሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እንደተተኮሱ እስካሁን አልታወቀም ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
በግንቦት ወር ብቻ በኪዬቭ ላይ የደረሰ 14ተኛው ጥቃት መሆኑ ተነግሯል።
15 ወራትን በዘለቀው ጦርነት ሞስኮ ከሁለት ወራት ወዲህ የአየር ድብደባ አጠናክራለች።
ጥቃቱም በዋናነት ወታደራዊ ስፍራዎች እና ቁሳቁሶች ላይ ያነጣጠረ ነው።