አውሮፕላኑ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት አብዬ ግዛት ውስጥ ነው የተከሰከሰው
ንብረትነቱ የሩሲያ የሆነ እቃ ጫን ካርጎ አውሮፕላን በደቡብ ሱዳን መከስከሱ ተስመቷል።
አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን በሚወዛገቡባት አብዬ ግዛት ውስጥ የሚገኝ አጎክ አውሮፕላን ማረፊያ በማረፍ ላይ እያለ ነው የተከሰከሰው።
አውሮፕላኑ 4 የበረራ አባላትን ይዞ የነበረ ሲሆን፤ በአውሮፕላኑ ላይ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ጉዳት ሳይደርስባቸው መውጣታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የሮም አሚር ግዛት አስተዳዳሪ ቾል ፎር ቾል፤ አደጋው ዛሬ ጠዋት ላይ መከሰቱን አስታውቀው፤ አውሮፕላኑ በማረፍ ላይ እያለ መከስከሱንም ገልፀዋል።
የአደጋው መንስዔ እንዲጣራም ጁባ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግስት የቴክኒክ ድጋፍ መጠየቃቸውን ነው አስተዳዳሪው ያስታወቁት።
ዛሬው አደጋ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተደጋጋሚ አደጋዎችን ተከትሎ የሩሲያ አንቶኖቭ አውሮፕላን በሀገሪቱ የኤር ክልል ላይ እንዳይበር ከከለከሉ 3 ወራ በኋላ ነው ተከሰተው።