አሳ አጥማጆች ባህር ላይ ያገኙትን መጠጥ ጠጥተው ሞቱ
ባለስልጣናት በጠርሙሱ ውስጥ የነበረውን ፈሳሽ ይዘት እየመረመሩ ናቸው
የሲርላንካ ባህር ኃይል ለጋዜጠኞች እንደተናገረው አሳ አጥማጆቹ ያገኙት ጠርሙስ ውስጥ የነበረውን ፈሳሽ አልኮል ነው ብለው በማሰብ ጠጥተውታል
አሳ አጥማጆች ባህር ላይ ያገኙትን መጠጥ ጠጥተው ሞቱ
አራት ሲርላንካውያን አሳ አጥማጆች በባህር ላይ በነበሩበት ወቅት ባገኙት ጠርሙስ ውስጥ የነበረ ምንነቱ ያልታወቀ መጠጥ ጠጥተው ህይወታቸው ሲያልፍ ሌላ አንድ ደግሞ በጽኑ ህመም ውስጥ እንደሚገኝ ቢቢሲ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ አሳ አጥማጆቹ ከጠረፍ 320 ማይል ርቀት ላይ ጉዞ እያደረጉ በነበረበት ወቅት ነው ጠርሙሱን ያገኙት።
የሲርላንካ ባህር ኃይል ለጋዜጠኞች እንደተናገረው አሳ አጥማጆቹ ያገኙት ጠርሙስ ውስጥ የነበረውን ፈሳሽ አልኮል ነው ብለው በማሰብ ጠጥተውታል።
የሲርላንካ የአሳ እና አኩያቲክ ሀብቶች ዳይሬክተር ጀነራል ሱዛንታ ካዋቴ ባህር ኃይል ወደ ባህር ዳርቻ ሊያመጣ ጥረት አድርጎ ነበር ብለዋል። ዳይክተሩ እንደገለጹት ባህር ኃይሉ ወደ መሬት ለመድረስ በቂ ሰአት ባለመኖሩ ባህር ላይ እያሉ የህክምና እርዳታ አድርጎላቸዋል።
ክዋቴ አሳ አጥማጆቹ ሌሎች ጠርሙሶችን በአካባቢው ለሌሎች አሳ አጥማጆች አሰራጭተዋል ብለዋል። ክዋቴ እንዳሉት ለእነዚህ ለማሳወቅ ጥረቶች ተደርገዋል።
ክስቱቱ ከሲርላንካ ዋና ከተማ ኮልምቦ በ193 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የጠረፍ ከተማ በህይወት ያሉትን ወደ መሬት አምጧቸው የሚል ተቃውሞ አስነስቷል።
ባለስልጣናት በጠርሙሱ ውስጥ የነበረውን ፈሳሽ ይዘት እየመረመሩ ናቸው።