አሜሪካ በምስራቅ እስያ እና በደቡብ ቻይና ባህር ጉዳይ ለምን ትሰጋለች?
አሜሪካ ከግዛቷ ውጪ በርካታ ቁጥር ያለው ወታደር እንዲሁም የጦር መሳርያ በአይነት እና በብዛት ያሰፈረችው በዚህ ቀጠና ነው
ከሰሞኑ ጃፓን ደቡብ ኮርያ እና አሜሪካ በጋራ ያደረጉት በአይነቱ ከፍተኛ የተባለው የጦር ልምምድ ዛሬ ይጠናቀቃል
አሜሪካ ደቡብ ኮርያ እና ጀፓን ለቀናት ሲያደርጉት የሰነበቱት በአይነቱ ከፍተኛ የተባለ የጦር ልምምድ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡
በባህር እና በአየር እንዲሁም የሰርጓጅ መርከብ ጥቃትን ለመከላከል በሚያስችሉ ወታደራዊ ስትራቴጂዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተከናወነው የጦር ልምምድ እስከዛሬ ከነበሩት ልምምዶች ዘመናዊ እና ግዙፍ የጦር መሳርያዎች ጥቅም ላይ የዋሉበት ነው፡፡
አሜሪካ ከሰሜን ኮርያ እና ከቻይና አለብኝ ላለቸው ስጋት ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ ከቀጠናው አጋሮቿ ጋር የምታደርገው ወታደራዊ ልምምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነቱ እያደገ ይገኛል፡፡
ለመሆኑ አሜሪካ በምስራቅ እስያ እና በደቡብ ቻይና ባህር ጉዳይ የምትፈራው ለምንድን ነው?
የምዕራቡ ሀያላን እና የሩቅ ምስራቋ ቻይና ከሚሻኮቱባቸው የአለም ሰትራቴጂካዊ ስፍራዎች አንዱ ነው የደቡብ ቻይና ባህር።
አካባቢው አሜሪካ ደቡብ ኮርያ እና ጃፓን ለመሳሰሉ ሀገራት የጦር መሳርያ ድጋፍ ከማድረግ አንስታ በአካል ወታደሮቿን እና የጦር መረከቦቿን በማስፈር በቀጥታ የምትሳተፍበት ፍጥጫ ሆኗል።
ከዚህ ባለፈም አሜሪካ ከግዛቷ ውጪ በርካታ ቁጥር ያለው ጦር መሳርያ በአይነት እና በብዛት ያሰፈረችው ጃፓን ላይ መሆኑን ለተመለከተ በቀጠናው ያላት ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎት ምን ያከል አንገብጋቢ መሆኑን ያስተውላል ።
ዋሽንግትን ቀጠናው ላይ ላላት ፍላጎት እንዲሁም ቢጄንግን ለመገዳደር በዘረጋቸው ስትራቴጂ ከደቡን ኮርያ እና ጃፓን ባለፈ ታይዋን እና አውስታራሊያ ከዛኛው የአለም ክፍል ደግሞ ብሪታንያ ዋነኛ አጋሯ ናቸው።
ከሰሞኑ በሁለቱ የእስያ ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የተደረገው ከፍተኛ የጦር ልምምድ በአካባቢው ያለውን ውጥረት ከፈ የሚያደርግ በመሆኑ ሁነቱን ተንተርሰው በቀጣይ የሚጠበቀውን በትንታኔ የሚስቀምጡ ጸሀፊዎች በርከት ብለዋል።
የደቡብ ቻይና ባህር እና ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታው
ይህ ስፍራ ቻይና ሁለት አይኗን ከድና የማተኛበት በንቃት የምትከታተለው ነው የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋን በግዜ ሂደት ለመጠቅለል ባላት ፍላጎት፤ እንዲሁም የደቡብ ኮርያ እና የጃፓን ከአሜሪካ ጋር ያለ ወታደራዊ አጋርነት ለብሔራዊ ደህንነቷ ስጋት አደርጎ የሳለ የውጭ ጉዳይ ፖሊስን የያዘቸበት ነው።
በስፍራው ያለው የነዳጅ እና የአሳ ከፍተኛ ምርትም በቀላል የሚታይ አይደለም 40 በመቶ የአለም የተፈጥሮ ጋዝ ከህንድ አና ከመካከለኛው ምስራቅ መነሻውን አድርጎ በዚህ ባህር በኩል ያልፋል፡፡
በዚህ አካባቢ የሚተላለፈው አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴ 3 ትሪሊዮንን የሚሻገር ነው በህንድ እና በፓስፊክ ውቅያኖስ መተላለፍያ እሯሷን እንደ ማእከላዊ የንግድ መነሻ ለማድረግ አቅድ ያላት ቤጂንግ ይህን ስፍራ መቆጣጠር ለእቅዷ መሳካት የማእዘን ዲጋን እንደሆነ ታምናለች።
ይህን የቻይና ሀሳብ አጥብቃ ስትቃዎም የከረመችው አሜሪካም ብትሆን በዚህ መስመር በ100 ቢሊዮን ዶላሮች የሚገመት ሸቀጥ ታስተላልፈበታለች፡፡ ይሁንና ለዋሽንግተን ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ይልቅ ከቻይና ጋር ለምትገኝበት የበላይነት እሽቅድደም በሚዛን ማስጠበቂያነቱ ስፍራው ያለው ጠቀሜታ ያደላል።
ሁለቱ ሀገራት በገልጽ ከሚገኙበት ሽኩቻ ባለፈ ቬትናም ፊሊፒን እና ማሌዢያ እንዲሁም ታይዋን የቦታው ይገበኛል ጥያቄ አላቸው አነዚህ ሀገራት ደግሞ አንዳንዴ በግልጽ ሌላ ገዜ ደግሞ በድብቅ የአሜሪካን አጀንዳ በውሀው ላይ የሚያራምዱ ናቸው።
ወደ ፓስፊክ ውቅያኖስ በሚያሻግረው መንገድ የዋሽንግተን የስፍራው ጠንካራ አጋር ታይዋን አለቸ ቤጂንግ ይህን ተጽእኖ ለመቋቋም በስፍራው በሚገኙ ደሴቶች የጦር ሰፈሮችን ብታቆምም የሀገራት የጦር ልምምድ ተሳትፎ ከፍ እያለ መምጣት ግን ሰግታትነቱ ዘቅ አላለም።
በቅርቡ በአሜሪካ እጅ የነበረውን የባሀር ሀይል የበላይነት በቴክኖሎጂ በጦር መሳርያ ብዛት እና በሌሎችም መስፈርቶቸ ጠንካራ የባሀር ሀይል በመገንባት ደረጃውን የነጠቀችው ቤጂንግ ከባይደን አስተዳደር በተስፋፊነት እና በሰጋትነት ጥርስ ካስነከሱባት አጀንዳዎች መካከል አንድኛው ነው።
በመሆኑም መሰል የዋሸንግተን አጋር ሀገራት በቀጠናው የሚያደርጉት ወታደራዊ ልምምድ የቤጂንግን ስጋትነት ለመከላከል ተጨማሪ አቅምን የሚፈጠር ነው እና ተቀባይነቱ ከፍተኛነው።
አሜሪካ በዚህ ስፍራ በተጠንቀቅ እየተከታተለች የምትገኝው ሌላው ጉዳይ ሰሜን ኮርያን ይመለከታል።
በቅርብ ግዝያት ግዙፍ አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳኤል የሙከራ አቅሟን እያሳደገች የምትገኝው ፒዮንግያንግ ለአሜሪካ ወታደሮች በስፍራው መኖር ተጨማሪ ምክንያት ናት።
ይህን ስጋት በቅድሚያ የሚጋሩት ደቡብ ኮርያ እና ጃፓን ሉአላዊነታቸውን ከጥቃት ለመከላከል ከአሜሪካ ጋር መወዳጀት ብቸኛ የመዳኛ መንገዳቸው አድርገው ወስደዋል።