ፓሪስ የዓለማችን የኤአይ መዲና መሆን ትፈልጋለች
ፈረንሳይ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚኒስትር ሾመች፡፡
የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ ያለችው ፈረንሳይ ከፓሪስ ኦሎምፒክ መስተንግዶ በኋላ ወደ ቀድሞ የፖለቲካ ትኩሳቷ ተመልሳለች፡፡
በድንገት ካቢኔያቸውን በመተን አዲ የህግ አውጪ ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ያደረጉት ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አዲስ ካቢኔ በማዋቀር ላይ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንቱ በአዲሱ ካቢኔያቸው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሚኒስትር ሾመዋል፡፡
የሀርቫርድ ዩንቨርሲቲ ምሩቅ የሆኑት ክላራ ቻፓዝ ደግሞ አዲ የተቋቋመውን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሚኒስቴር እንዲመሩ ተሹመዋል፡፡
ክላራ ቻፓዝ ከዚህ በፊት የፈረንሳይ ቴሌኮሙንኬሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያን በስራ አስኪያጅነት የመሩ ሲሆን በስኬታማነታቸው ይተወቃሉ ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ማክሮን ቻፓዝን በሚኒስትር የሾሙት ፓሪስን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል የማድረግ ዓለማ ስላላቸው እንደሆነ ዩሮ ኒውዝ ዘግቧል፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ባለቤት ብሪጅት ማክሮን ጾታቸው ወንድ ነው ብለው ዘገባ የሰሩ ጋዜጠኞች 8 ሺህ የሮ ካሳ እንዲከፍሉ ተፈረደባቸው
ዘገባው አክሎም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ዓለማችንን እየመራች ያለችውን አሜሪካ ለመፎካከር ፈረንሳይ እቅድ እንዳላትም ጠቅሷል፡፡
የዓለማችን የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ሰው ሰራሽ አስተውሎት ጉባኤ በለንደን እና ሴኡል የተካሄደ ሲሆን ፓሪስ ሶስተኛውን ጉባኤ የፊታችን የካቲት የማዘጋጀት እቅድ እንዳላትም ተገልጿል፡፡
ቻት ጅፒቲ አሁን ላይ በዓለማችን ካሉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ውጤቶች ቀዳሚው ሲሆን ፈረንሳይም ሚስትራል የተሰኘውን ተመሳሳይ ኤአይ አስተዋውቃለች፡፡