ናይጀሪያ ከ10 ዓመት በፊት ከአንድ የቻይና ኩባንያ ጋር የኢኮኖሚ ዞን ለመገንባት ስምምነት የነበራት ቢሆንም ስምምነቱ በህዝብ ቁጣ ምክንያት ተሰርዟል
የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ሶስት ጀቶች በፈረንሳይ ታሰሩ፡፡
በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ እና ህዝብ ያላት ናይጀሪያ ፕሬዝዳንት መንቀሳቀሻ ናቸው የተባሉ ሶስት ጀቶች በፈረንሳይ ታግደዋል፡፡
ለቀላል ጥገና በሚል ወደ ፈረንሳይ የሄዱት እነዚህ ጀቶች ጥገናቸውን ጨርሰው ሊንቀሳቀሱ ሲል የፍርድ ቤት እግድ ወጥቶባቸዋል፡፡
የናይጀሪያ ፕሬዝዳንት ቲንቡ መንቀሳቀሻ ናቸው የተባሉት እነዚህ ጀቶች ላይ የፍርድ ቤት እግድ ያወጣው የቻይናው ዞንግሻን ፉቼንግ የተባለ ኩባንያ ነው፡፡
ይህ የኢንዱስትሪ ኩባንያ በፈረንጆቹ 2015 ላይ ከናይጀሪያዋ ኦጉን ክልል ጋር የኢኮኖሚ ዞን ለማቋቋም የስራ ስምምነት ተፈራርሞ ነበር፡፡
የናይጀሪያ አየር መንገድ መንገደኞችን የተሳሳተ ኤርፖርት ማራገፉ ተገለጸ
ይሁንና የኢኮኖሚ ዞን ይገነባበታል በተባለው ቦታ እና አጠቃላይ እቅዱ ዙሪያ የህዝብ ቁጣ መበርታቱን ተከትሎ ይህ ስምምነት በ2016 ተሰርዞ ነበር፡፡
ስምምነቱ የተሰረዘበት ይህ የቻይና ኩባንያም ኪሳራ ደርሶብኛል በሚል የናይጀሪያ መንግስት ካሳ እንዲከፍለው ጠይቆ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ኩባያው ካሳ እንዲከፈለው ቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ሀገሪቱ በውጭ ሀገራት ያላት ንብረቶች እንዲታገዱ በፈረንሳይ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ ባሉ ፍርድ ቤቶች ክስ መስርቷል፡፡
በዚህ የፍርድ ቤት ክስ መሰረትም በየሀገራቱ ያሉ የናይጀሪያ መንግስት ንብረቶች እየታገዱ ሲሆን ወደ ፓሪስ ለጥገና ያመሩ የፕሬዝዳንቱ መንቀሳቀሻ ጀቶች ሊታገዱ ችለዋል፡፡
የናይጀሪያ መንግስት በበኩሉ የቻይናው ኩባንያ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማቅረብ ጉዳት እንደደረሰበት እያስመሰለ ነው ብሏል፡፡
ዞንግሻን ፉቼንግ ከኦጉን ክልል ጋር የገባው ስምምነት በመፍረሱ የተጎዳው ምንም ነገር ያለም የሚለው የናይጀሪያ መንግስትኩባንያው አንድ ስንዝር ግንባታ አልጀመረም ሲል አስታውቋል፡፡