ፖለቲካ
ፈረንሳይ የመንግስት ወጪን በ 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዩሮ ልትቀንስ ነው
የፈረንሳይ መንግስት ከ10 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጪውን እንደሚቀንስ ገልጿል
መንግስት በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ ላይ ያደርገው የነበረውን ከፍተኛ ድጎማ በመቀነስ ነው ወጪን እቀንሳለሁ ያለው
የፈረንሳይ መንግስት ለፓርላማ አባላት በላከው የመጀመሪያ የበጀት ግምት መሰረት በ2024 በነዳጅ እና በኤሌትሪክ ላይ ከፍተኛ ድጎማዎችን በመቀነስ 4 ነጥበሰ 2 ቢሊዮን ዩሮ (4 ነጥብ 71 ቢሊዮን ዶላር) ያነሰ ወጪ እንደሚያወጣ ይጠብቃል።
የበጀት ሚንስትሩ ገብርኤል አታታል እንደተናገሩት "ከ10 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወጪ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ይቀንሳል"።
ሚንስትሩ የዋጋ ንረት ወደ 3 ነጥብ 5 በመቶ መቀነስ ማለት እንደሆነ አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፈረንጆቹ 2022 የድጋሚ ምርጫ ቅስቀሳ አጋማሽ ላይ ሸማቾች እየጨመረ ከሚሄደው የኃይል ክፍያ ለመጠበቅ የኤሌክትሪክ ዋጋን ለመደጎም ሰፊ እቅዶችን አውጥተዋል።
የኃይል ዋጋዎች መቀነስ ሲጀምር እርምጃዎች በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ይቋረጣሉ ተብሏል።
ይህም በሚቀጥለው ዓመት ወደ 14 ቢሊዮን ዩሮ የሚጠጋ ወጪ ቀንሷል ብለዋል ሚንስትሩ።
"ልዩ የቀውስ ወጪን እያቆምን እና ቁጠባ እያሳደረግን ነው" ብለዋል።