በፈረንሳይ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ 600 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በፈረንሳይ የ17 ዓመት ታዳጊ በፖሊስ መገደሉን ተአትሎ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል
ፕሬዝደንት ማክሮን አስቸኳይ የጸጥታ ስብሰባ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት ጉባኤን አቋርጠዋል
ሶስተኛ ቀኑን በያዘው የፈረንሳይ ተቃውሞ ውጥረቱ በመጨመር ተቃዋሚዎች ከፖሊስ ጋር ግብግብ ገብተዋል።
ፓሊስ የ17 ዓመት ታዳጊን መግደሉ በሀገሪቱ ቁጣን ቀስቅሷል። በሦስተኛው ምሽት በተነሳው ሁከትና ብጥብጥ መንግስት ጸጥታን ለመመለስ ከ600 በላይ ሰዎች አስሯል።
በፓሪስ አቅራቢያ ባለ አካባቢ ተቃዋሚዎች ማዘጋጃ ቤት ላይ እሳት ለኩሰው በአውበርቪሊየር የአውቶቡስ መጋዘን አቃጥለዋል።
የፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ የእሳት ቃጠሎ እና አንዳንድ መደብሮች ተዘርፈዋል።
በሜዲትራኒያን ወደብ በሆነችው ማርሴይ ፖሊሶች በከተማው ውስጥ ሁከት የሚፈጥሩ ቡድኖችን ለመበተን ጥረት አድርገዋል ሲሉ የግዛቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አስቸኳይ የጸጥታ ስብሰባ ለማድረግ ፈረንሳይ በአውሮፓ ፖሊሲ አውጭነት ትልቅ ሚና ከምትጫወትበት የአውሮፓ ህብረት ጉባኤ አቋርጠው ወደ ፓሪስ ተመልሰዋል።
ተቃውሞውን ለመቀልበስ 40 ሽህ የሚሆኑ ፖሊሶች ተሰማርተዋል ሲል ታይምስ ዘግቧል።
ፖሊስ 667 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፤ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትሩ ከእነዚህ ውስጥ 307 የሚሆኑት በፓሪስ ክልል ብቻ የተያዙ ናቸው ብለዋል።
የሀገሪቱ ፖሊስ ቃል አቀባይ እንዳስታወቀው 200 የሚደርሱ የፖሊስ አባላት ቆስለዋል።
ህዝብ ላይ ስለደረሰ ጉዳት ምንም አይነት መረጃ አልተገኘም።