ዩክሬን ከፈረንሳይ የተሰጡ የውጊያ ታንኮች እየጠቀሟት እንዳልሆነ ገለጸች
የፈረንሳይ ታንኮች በጭቃ ላይ መጓዝ አለመቻል እና በሩሲያ ጦር በቀላሉ እየተመቱ ነው ተብሏል
ፈርንሳይ ለዩክሬን የጦር ታንኮችን ከሰጡ የአውሮፓ ሀገራት መካከል አንዷ ሀገር ነች
ዩክሬን ከፈረንሳይ የተሰጡ የውጊያ ታንኮች እየጠቀሟት እንዳልሆነ ገለጸች
የፈረንሳይ ታንኮች በጭቃ ላይ መጓዝ አለመቻል እና በሩሲያ ጦር በቀላሉ እየተመቱ ነው ተብሏል
ፈርንሳይ ለዩክሬን የጦር ታንኮችን ከሰጡ የአውሮፓ ሀገራት መካከል አንዷ ሀገር ነች
ዩክሬን ከፈረንሳይ የተሰጡ የውጊያ ታንኮች እየጠቀሟት እንዳልሆነ ገለጸች፡፡
ለአንድ ሳምንት በሚል የተጀመረው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት 16ኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን በርካታ ክስተቶችን አስተናግዷል፡፡
ዩክሬን ከአሜሪካ እና አውሮፓዊያን ባሰባሰቧቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች አማካኝነት የሩሲያን ጦር ከግዛቷ ለማስለቀቅ ዘመቻ ላይ መሆኗን አስታውቃለች፡፡
ሩሲያን ከግዛቷ ለማባረር የጦር መሳሪጠያ ከሰጡ ሀገራት መካከልም ፈረንሳይ አንዷ ስትሆን ኤኤምኤክስ-10 የተሰኘው የጦር ታንኳን ለኪየቭ ሰጥታለች፡፡
የዩክሬን ወታደራዊ አመራሮች ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንዳሉት ከፓሪስ የተሰጣቸው የጦር ታንክ ብዙ እየጠቀማቸው እንዳልሆነ ተናግረዋ፡፡
ኤኤምኤክስ-10 የተሰኘው ይህ የጦር ታንክ በቅርብ ርቀት ያለን የጠላት ተቀጣጣይ ነገሮችን ለመምታት ጥሩ ቢሆንም በሩሲያ ታንኮች በቀላሉ እየተመታባቸው እና የታንኩ አሽከርካሪዎች እየተገደሉባቸው መሆኑነንም ወታደሮቹ አክለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ይህ ታንክ በፍጥነት ተንቀሳቅሶ ጥቃት እንዳይከፍት በጭቃ እና በሌሎች ምክንያቶች ከጥቅም ውጪ እየሆነ ነው ሲሉም ወታደራዊ አዛዦቹ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የዩክሬን ታንክ አሽከርካሪዎች ከፈረንሳይ የተለገሰውን የውጊያ ታንክ ለማሽከርከር የወሰዱት ስልጠና አጭር መሆኑ ሌላኛው ፈተና ነው ተብሏል፡፡
ከአሜሪካ እና ብሪታንያ የተለገሱት የጦር ታንኮች ግን በአንጻራዊነት የተሻሉ ሆነው መገኘታቸውም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ዩክሬን የጀመረችው የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ ጥሩ ድል እያስገኘላት መሆኑን የገለጸች ሲሆን በተለይም በባክሙት ግንባር ወታደሮቿ ወደ ፊት እየገሰገሱ ናቸው ብላለች፡፡
ሩሲያም በተመሳሳይ ድል እየቀናት መሆኑን፣ የዩክሬን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ መክሸፉን በመናገር ላይ ናት፡፡