ፈረንሳይ አምባሳደሮቿን የጠራችው አውስትራሊያ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን የሰብማሪን ግዥ ውል በመሰዟ ነው ተብሏል
ፈረንሳይ አምባሳደሮቿን የጠራችው አውስትራሊያ ከፈረንሳይ ጋር የነበራትን የሰብማሪን ግዥ ውል በመሰዟ ነው ተብሏል
የአሜሪካ የረጅም ጊዜ አጋር የሆነችው ፈረንሳይ ባልተጠበቀ ሁኔታ በአሜሪካ እና በአውስትራሊያ ያሉ አምባሳደሮቿን መጥራቷ ረጅሙን ግንኙነት ያሳጥረዋል ተብሏል፡፡
ፈረንሳይ ይህን ርምጃ የወሰደችው፣ አውስትራሊያ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ ጋር በመሆን አዲስ ግንኙነት በመመስረታቸውና ይህም አደጋ በመደቀኑ ምንክያት ነው ተብላል፡፡ ፈረንሳይ አደጋ የወለደ ግኝኑነት ነው ያለችው፤ከአውስትራሊያ ጋር የነበራት የሰብማሪን ስምምት እንዲሰረዝ በማድረጉ ነው፡፡
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ድሪያን እንደተናገሩት በፕሬዝዳንት ማክሮን ጥያቄ አማካኝነት አምባሳደሮቹ ለምክክር ወደ ፖሪስ እንዲመጡ መወሰናቸውንና፤ይህም የሆነው አሜሪካና አውስትራሊያ ባደረጉት ለየት ያለ ስምምነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸውን ሀገራቸው ከፈረንሳይ ሰብማሪን ለመግዛት ያላት እቅድ በመሰረዟ ምክንያት ፈረንሳይ ቅር ሊላት እንደሚችል እንደሚረዱና ከፈረንሳይ ጋር አሁን ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
አሜሪካም ጉዳዩ ሊያበሳጭ እንደሚችል እንደምትረዳ ገልጻለች፡፡ የአሜሪካዋ ማሪስ ፓይን ይህ ጉዳይ ለመፍታት ቀላል እንደማይሆን ተናግረዋል፡፡
ነገርግን ማሪስ ፓይን ፓሪስ ካሉ አጋሮቻችን ጋር በቅርበትና ገምቢ በሆነ መልኩ እንሰራልን ብለዋል፡፡
ፈረንሳይ፣ አውስትራሊያ ከፈረንሳይ ጋር ያላት የግዥ ስምምነት ካፈረሰች በኋላ አውስትራሊያ በአውሮፓ ህብረት የምታደርገውን የንግድ ውይይት እንደማታምን ገልጻለች፡፡
ፈረንሳይ የአውስትራሊያን እርምጃ ከጀርባ የመውጋት ነው ብላለች፡፡