የጊኒ መፈንቅለ መንግስት መሪ ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የፈረንሳይ ጦር አባል ነበር ተባለ
ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የጊኒ ልዩ ሀይልን እንዲመራ በፕሬዚዳት አልፋ ኮንዴ ነበር የተሾመው
በኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የሚመራው መፈንቅላ መንግስት ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን ከስልጣን በማንሳት በቁጥጥር ስር አውሏል
የጊኒ መፈንቅለ መንግስት መሪ ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ በፈረንሳይ ጦር ውስጥ እንደበረ ተነገረ።
ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የጊኒ ልዩ ሀይልን ከመቀላቀሉ እንደ ፈረንጆቹ እስከ 2018 ድረስ በፈረንሳይ ጦር ውስጥ ሲያገለግል ነበር ተብሏል።
የጊኒ ልዩ ሀይል በ2018 መመስረቱን ተከትሎ ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ ከፈረንሳይ ጦር በመውጣት ልዩ ሀይሉን እንዲመራ በፕሬዚዳት አልፋ ኮንዴ አማካኝነተ ጥሪ ተደርጎለት ነው ልዩ ሀይሉን የተቀላቀለው።
የጊኒ ልዩ ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ የሰለጠነ እና ታጠቀ ወታደራዊ ሀይል ሲሆን፤ ኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ ናቸው በመመራት ላይ የሚገኙት።
ልዩ ሀይሉ በትናንትናው እለት ባደረገው መፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ኮንዴን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ወታደሮች የሃገሪቱን ህገ መንግስት ማገዳቸውንና ስልጣን መቆጣጠራቸውን እንዲሁም በረራዎችን ማገዳቸውን አሳውቀዋልም ተብሏል።
በኮሎኔል ማማዲ ደንቦያ የሚመራው መፈንቅላ መንግስት ምንመ እንኳ ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴን በቅጥጥር ስር ቢያውልም፤ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ አልሆነም ተብሏል።
መፈንቅለ መንግስቱን ያካሄደው ቡድን እስካሁን ብሄራዊ ቤተ መንግስት፣ ማእከላዊ ባንክ እና ካማ ሆቴልን የተቆጣጠረ ሲሆን፤ በኮናክሬ ጎዳናዎች ላይ እስካን ግጭቶች ቀጥለዋለ ተብሏል።
አልፋ ኮንዴ በፈረንጆቹ በ2017 የአፍሪካ ህብረትን በሊቀመንበርነት መርተዋል። ባሳለፍነው ጥር ወደ ደቡብ አፍሪካ አቅንተው የነበሩት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ጊኒን እንደጎበኙና በፕሬዝዳንት ኮንዴ አቀባበል እንደተደረገላቸው የሚታወስ ነው።