የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂያን ካስቴክስም የዬርዳኖስ ጉብኝታቸውን ሰርዘዋል
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤ ማክሮን ወደ ማሊ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰረዙ፡፡
ማክሮን ወደ ምዕራባ አፍሪካዊቷ አገር ማሊ ከዛሬ ጀምሮ ለይፋዊ የስራ ጉብኘት እንደሚጓዙ ጽህፈት ቤታቸው ገልጾ ነበር፡፡
ኢማኑኤል ማክሮን በጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ
ይሁንና ፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል አዲስ ክልከላ ማውጣቷን ተከተሎ ጉዟቸውን እንደሰረዙ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በእቅዳቸው መሰረት ወደ ማሊ አቅንተው ቢሆን ኖሮ ከማሊ ወታደራዊ የሽግግር ፕሬዝዳንት ኮሎኔል አስሚ ጎይታ ጋር ይመክሩ ነበር፡፡
በተጨማሪም ማሊ ውስጥ ከሚገኘው የሃገራቸው ጦር ጋር አዲሱን የፈረንጆች ዓመት ገናን ለማክበር ቀጠሮ ይዘው ነበር፡፡
ማክሮን ኮሎኔል አስሚ ጎይታን የጋናው ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ እና የቻዱ ፕሬዝዳንት መሃማት እድሪስ ዴቢ ባሉበት ለማግኘት ቀጠሮ ይዘውም ነበር፡፡ ሆኖም የቻዱ መሪ መሃማት እድሪስ ዴቢ ሃሳቡን ተቃውመውታል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ጂያን ካስቴክስም ወደ መካከለኛው ምስራቅ ዮርዳኖስ ለመጓዝ ይዘውት የነበረውን የጉዞ መርሃ ግብር በተመሳሳይ ምክንያት ሰርዘዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ቤሩት ለማቅናት አቅደው የነበረው በቀጣይ ሳምንት ነበር፡፡