ልዩልዩ
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ ተመቱ
ፕሬዝደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኝ ደሮም በተባለች ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው የተመቱት
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን የስራ ጉብኝት ላይ እያሉ በጥፊ መመታታቸው ተነግሯል።
ፕሬዚደንቱ በደቡብ ምስራቅ ፈረንሳይ በምትገኝ ደሮም በተባለች ከተማ ጉብኝት በማድረግ ላይ እያሉ ነው ፊታቸው ላይ በጥፊ የተመቱት።
በማህበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ላይ የተለቀቀ ተንቀሳቃሽ ምስል እንደሚያሳው ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በተከለለ አጥር ውስጥ የነበሩ ሰዎችን ሰላም ለማለት ጎራ ሲሉ ነው ጉዳዩ የተከሰተው።
ከብረት መከለያ አጥሩ ጀረባ ቆመው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንድ ግለሰብ ፐሬዝደንቱን ፊታቸው ላይ በጥፊ ሲመታም ተስተውሏል።
https://twitter.com/AlexpLille/status/1402237903376367627
ፕሬዝደንት ማክሮንን በጥፊ የመታው ግለሰብም ወዲያውኑ በፀጥታ አካላት በቁጥጥር ሲር የዋለ ሲሆን፤ ፐሬዝደንቱም በፍጥነት ስፍራውን ለቀው ሄደዋል።
የፈረንሳይ ሚዲያዎች ዘገባ እንደሚያመለክተው ፣ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ፕሬዝደንት ማክሮን በጥፊ መመታታቸውን ተከትሎ "ማክሮኒዝም ይውደም" የሚሉ ድምጾች ሲሰሙ እንደነበረም ነው የተነገረው።