ፈረንሳይ ኒጀርን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት አምባሳደሯ በሀገሪቱ እንደሚቆዩ ገለጸች
ፈረንሳይ ኒጀርን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው በኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደር በሀገሪቱ እንደሚቆዩ ገልጻለች
ፈረንሳይ እና ዲፕሎማቾቿ በቅርብ ወራት ውስጥ ከሱዳን እስከ ኒጀር ድረስ የተለየ ችግር አጋጥሟቸዋል"ሲሉ ማክሮን ተናግረዋል
ፈረንሳይ ኒጀርን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው በኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደር በሀገሪቱ እንደሚቆዩ ገልጻለች።
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ማክሮን በፖሪስ አምባሳደሮችን ሰብስበው ባደረጉት ንግግር ምንም እንኳን የፈረንሳዩ አምባሳደር ሲሊቪያን አቴ ኒጀርን ለቀው እንዲወጡ የ48 ሰአታት ገደብ የተሰጣቸው በሆንም ለቀው እንደማይወጡ አረጋግጠዋል።
ፈረንሳይ እና ዲፕሎማቾቿ በቅርብ ወራት ውስጥ ከሱዳን እስከ ኒጀር ድረስ የተለየ ችግር አጋጥሟቸዋል"ሲሉ ማክሮን ተናግረዋል።
በፈረንሳይ እና በኒጀር ጎረቤቶች በተወገዘው የሀምሌው መፈንቅለ መንግስት፣ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት መሃመድ ባዙም እና ቤተሰቦቻቸው ከስልጣን ወርደው ታስረዋል።
ባለፈው አርብ የኒጀር የውጭ ጉዳይ ማኒስትር የፈረንሳይ መንግስት ከኒጀር መንግስት ከኒጀር መንግስት ጥቅም ቀተቃራኒ መቆሙን ጠቅሶ አምባሳደር ኢቴ በ48 ሰአታት ውስጥ ሀገር ለቀው እንዳወጡ ትዕዛዝ አስተላልፋ ነበር።
ፈረንሳይ መፈንቅለ መንግስቱን እንደምታወግዝ እና በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡትን ባዙምን ትደግፋለች ብለዋል ማክሮን።
የምዕራብ አፍራካ ሀገራት ጥምረት የሆነው ኢኮዋስ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የተቆጠሠጠረው ጁንታ ባዙም የማይመልስ ከሆነ ወታደራዊ ጣልቃገብነት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።