ፕሬዝዳንት ባዙም ከውጭ ሀገር መሪዎችና ድርጅቶች ጋር ባለቸው "ግንኙነት" እንደሚከሰሱ ተነግሯል
በኒጀር ከሳምንታት በፊት መንግስት ገልብጦ ስልጣን የጨበጠው ጁንታ ፕሬዝዳንት መሀመድ ባዙም ከውጭ ሀገር መሪዎችና ድርጅቶች ጋር ባለቸው ግንኙነት በሀገር ክህደት ሊከሳቸው እንደሆነ አሳውቋል።
የመፈንቅሉ መሪዎች ፕሬዝዳንቱ የኒጀርን የውስጥና የውጭ የደህንነት ፍላጎቶች ቸል ማለታቸውን የሚያሳዩ አስፈላጊ ማስረጃዎች መሰብሰባቸውን ተናግረዋል።
እርምጃውን የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት፣ የመንግስታቱ ድርጅትና አሜሪካ "ቀውሱን የሚያባብስ" ሲሉ አውግዘውታል።
ተመድ ለማቅረብ የተፈለገው ክስ የሚያሳስብ እንደሆነ ገልጾ፤ ፕሬዝዳንት ባዙም በአፋጣኝ እንዲለቀቁ ጥሪ አቅርቧል።
የመፈንቅለ መንግስቱ መሪዎች ፕሬዝዳንት ባዙምንና መንግስታቸውን አስረዋል።
የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ (ኢኮዋስ) በበኩሉ እርምጃውን "ቀስቃሽ" ብሎታል።
ኢኮዋስ በጁንታው መንግስት አቋም ባለፈው ሳምንት ተጠባባቂ ወታደራዊ ኃይል ለማቋቋም ውሳኔ አሳልፏል።
ቀውሱ ግዙፍ የዩራኒየም አምራች ለሆነችው ለኒጀር ብቻ አይተርፍም ተብሏል።
በቀጣናው እስላማዊ ሸማቂዎችን በመዋጋት ለምዕራባዊያን አጋር የሆነችው ሀገር ውጥቅጧ ከራስ የተረፈ ነው በሚል በስጋት ሸብቧል።