ኒጀር የፈረንሳይ አምባሳደር በ48 ሰአታት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች
እንደ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ ሁሉ በኒጀር የተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ጸረ-ፈረንሳይ እንቅስቃሴ እያየለ በመጣበት ወቅት ነው
በጁንታው የተሾመው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የፈረንሳይን አምባሳደር ለማባረር የተወሰነው ፈረንሳይ ከኒጀር ጥቅም በተቃራኒ በመቆሟ ነው ብለዋል
ባለፈው ሐምሌ ወር መፈንቅለ መንግስት በማድረግ ስልጣን የተቆጣጠረው የኒጀር ጁንታ የፈረንሳይ አምባሳደር ስሊቪያን ሊቴ ሀገሪቱን በ48 ሰአታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዟል።
በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር እና በቀድሞ ቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ በሻከረበት ወቅት ነው ጁንታው ይህን ውሳኔ ያሳለፈው።
እንደ ቡርኪናፋሶ እና ማሊ ሁሉ በኒጀር የተፈጸመው መፈንቅለ መንግስት ጸረ-ፈረንሳይ እንቅስቃሴ እያየለ በመጣበት ወቅት ነው። ፈረንሳይ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባች ነው ብለው የሚከሷትም አሉ።
በጁንታው የተሾመው የውጭ ጉዳይ ባወጣው መግለጫ የፈረንሳይ አምባሳደር ለማባረር የተወሰነው ፈረንሳይ ከኒጀር ጥቅም በተቃራኒ በመቆሟ ነው ብለዋል።
አምባሳደሩ አዲሱ የኒጀር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላቀረቡት የእንገናኝ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸው ተገልጿል።
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምላሽ አልሰጠም።
ኒጀር የአሜሪካ እና የጀርመን አምባሳደሮች ሀገሪቱን እንዲለቁ ማዘዟን የሚያመላክት ኦፊሴላዊ የሚመስል ደብዳቤም ተሰራጭቷል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግን ኒጀር እንዲህ አይነት ደብዳቤ አለመጿፋን አሳውቃኛለች ብሏል። "ለአሜሪካ መንግስት እንዲህ አይነት ጥያቄ አልቀረበም።"
ለጁንታው እና ለኒጀር የጸጥታ ኃይሎች ቅርብ የሆኑ አካላት እንዲለቁ የታዘዙት የፈረንሳይ አምባሳደር ብቻ ናቸው።
መፈንቅለ መንግስት በፈረንሳይ እና በኒጀር መካከል የነበረውን የቆየ ግንኙነት ወደ ከፋ ደረጃ አድርሶታል።