ቄሶች ከፈጣሪ ጋር ተነጋግረው እየዘነበ ያለው ዝናብ ቆሞ ፀሀይን ከተደበቀችበት እንዲያስወጡ በከንቲባው ማዘዙ ተሰምቷል
ቄሶች ጸሀይን እንዲያስወጡ ያዘዘው ከንቲባ።
በፈረንሳይ ኖርማንዲ ኮሎንስስ አነስተኛ ከተማ ከንቲባ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እና ዳመናማ የአየር ንብረት መማረራቸውን ተናግረዋል።
የክረምት ወቅት በጸሀይ ሙቀት የምንዝናናበት ወቅት ነበር የሚሉት እኝህ ከንቲባ ጸሀይ በዳመና መከለሏን ኮንነዋል።
በዚህም መሰረት ከንቲባው የከተማዋን ቄሶች ሰብስበው ጸሀይን ከተደበቀችበት አስወጡ ሲሉ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ ቄሶች ገነት ካለው አካል ጋር ተነጋግረው ጸሀይን እንዲያስወጡ ሲሉም አዘዋል።
ከንቲባው አክለውም እንደ ዘንድሮው አይነት ዝናብ በህይወት ዘመናቸው አይተው እንደማያውቁ ዝናቡ ሲዘንብ ሰማይ የተቀደደ ይመስላል ብለዋል።
227 ነዋሪዎች ያሏት ይህች አነስተኛ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ዳንኤል ማሬሬ " በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ዝናብ በከተማዋ እንዳይዘንብ አድርጉ" ሲሉ ቄሶቹን እንዳዘዙ ተሰምቷል።
"ይህን ውሳኔ በማስተላለፌ የከተማዋ ነዋሪዎች ያመሰግኑኛል" የሚሉት ከንቲባው በከተማችን ጸሀይ የግድ መውጣት አለባት ብለዋል ተብሏል።
የፈረንሳይ አየር ንብረት ባለስልጣን እንዳስታወቀው ከሆነ አሁን እየዘነበ ያለው የዝናብ መጠን ከዚህ በፊት ከነበረው ፍጹም የተለየ መሆኑን አስታውቋል።
አሁን የዘነበው ዝናብ መጠን መዝነብ ካለበት ገና 20 በመቶው ብቻ ነው ያለ ሲሆን ዝናብ መዝነብ እንደሚቀጥል ገልጿል።