በጠንቋይ የተሞኘው የፈረንሳይ ከተማ ከንቲባ
አግዴ የተሰኘችው የፈረንሳይ ከተማ በአውሮፓዊያን ለመዝናኛነት ተመራጭ ከተማ ናት
በዚች ከተማ ያለች አንድ ጠንቋይ ሴት የከተማዋን ከንቲባ ፍላጎቷን እንዲያሟላ ተጠቅማበታለች ተብሏል
በጠንቋይ የተሞኘው የፈረንሳይ ወቧ የባህር ዳርቻ አግዴ ከተማ ከንቲባ
አግዴ የተሰኘችው የባህር ዳርቻ ከተማ ስትሆን በፈረንሳይ በጎብኚዎች ከሚዘወተሩ ስፍራዎች መካከል ዋነኛዋ ናት፡፡
የሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ የምትገኘው ይህች ከተማ ዓመቱን በሙሉ ጸሀይ የሚወጣባት ከተማ በመባል የምትታወቅ መዝናኛ ከተማምነች፡፡
ይህች ከተማ በተለይም የወሲብ ከተማ በመባል የምትጠራ ሲሆን ጥንዶች ወደ ከተማዋ በመሄድ ለተወሰኑ ጊዜያት ያህል ፍቅረኛ በመቀያየር ለመደሰት የሚመርጧት ከተማ እንደሆነችም ይነገራል፡፡
ሶፊያ ማርቲኔዝ የተሰኘች ሴት የዚህ ከተማ ነዋሪ ስትሆን በጥንቆላ ስራዋ ታዋቂ ናት፡፡
ጊሌ ኢሮር የተሰኘው ግለሰብ ደግሞ የዚች ከተማ ከንቲባ ሲሆን ከዓመታት በፊት ወላጅ አባቱን በሞት አጥቷል፡፡
ከንቲባ ጊሌ ከጠንቋይ ሶፊያ ለረጅም ጊዜ የተለየ ግንኙነት አለው በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ከንቲባውን ለእስር የዳረገው ደግሞ ይህች ጠንቋይ ከዓመታት በፊት የሞተውን አባትህን እኔ ማውራት እችላለሁ ትለዋለች፡፡
መጀመሪያ ላይ የጠንቋይ ሶፊያን ሀሳብ ውድቅ ያደረገ ቢሆንም በተደጋጋሚ ባደረገችበት ጫና ምክንያት ሀሳቧን ይቀበላል፡፡
ይህች ጠንቋይም አባቱን እንደምታወራ እያንዳንዱን ሀሳብም ለዚሁ ከንቲባ አባትህ እንዲህ ብሏል እንዲህ አድርግ እያለች ስትነግረው እና ከንቲባውም ሀሳቡን መቀበሉ ተገልጿል፡፡
ጠንቋይ ሶፊያ ለሰራችው ውለታ በሚል ከንቲባው ወደ ታይላንድ እና ሌሎች ከተሞች እንድትዝናና ወጪዋን በመሸፈን፣ ዘመዶቿን ስራ ማስቀጠር እና ሌሎች ስጦታዎችን ሰጥቷል በሚል የሕዝብ ገንዘብ በማባከን ለእስር ተዳርጓል፡፡
ፈረንሳይ የፕሬዝዳንት ፑቲን የቀድሞ ሚስት ንብረትን አገደች
ፖሊስ ከከንቲባው በተጨማሪም ጠንቋይ ሶፊያንም ያሰረ ሲሆን ሴት እስረኞች አብራቸው እንዳትታሰር በመጠየቃቸው ለብቻዋ መታሰሯን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የከንቲባው ጠበቃ ለቢቢሲ እንዳለው ጠንቋይ የምትባለው በደንበኛው ለይ የረቀቀ የአዕምሮ ጨዋታ እንደተጫወተች እና ተጽዕኖ በመፍጠር አታለዋለች ብሏል፡፡
ከንቲባው የሷን ሀሳብ እንዲቀበል በደካማ ጎኑ በመግባት፣ ስለ ቤተሰቡ ጥልቅ ሚስጢር በማጥናት ለእሷ ጥቅም እንዲሰራ እንዳደረገችውም ጠበቃው ተናግሯል፡፡
ጉዳዩ በመላው ፈረንሳይ ትኩረት የሳበ ሲሆን በማሪን ለፐን የሚመራው የቀኝ አክራሪ ፓርቲ ከንቲባው የህዝብን ገንዘብ አባክኗል በሚል ስልጣን እንዲለቅ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡