ፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ያልወሰዱ 3 ሺህ የጤና ባለሙያዎችን ከስራ አገደች
ፕሬዝዳንት ማክሮን ሰራተኞች ቢያንስ አንዴ ክትባቱን እንዲወስዱ ያን ካልሆነ ግን ስራቸውን እንደሚያጡ ተናግረው ነበር
ፈረንሳይ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰራተኞቿ በግዴታ እንዲከተቡ አዛለች
ፈረንሳይ የኮሮና ቫይረስ ያልተከተቡ 3 ሺህ የጤና ባለሙዎችን ከስራ አገደች።
ከአውሮፓ አገራት በኮቪድ ክፉኛ ከተጎዱ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ፈረንሳይ የጤና ባለሙያዎች እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች የግድ ክትባቱን አንዲወስዱ ውስኔ አስተላልፋለች።
በዚህም መሰረት ክትባቱን ያልወሰዱ 3 ሺህ የጤና ባለሙያዎችን ከስራ ማገዷን አስታውቃለች።
በአጠቃላይ አገሪቱ 2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሰራተኞች የግድ የኮሮና ቫይረስ ክትባት እንዲከተቡ ትዕዛዝ ሰጥታለች።
ክትባቱን የመውሰድ ግዴታ የተጣለው በሁሉም የህክምና ዶክተሮች፤ነርሶች፤ በጎ ፈቃደኛ የጤና ባለሙያዎች እና ሌሎች መሰል ባለሙያዎች ላይ እንደሆነ ፍራንስ 24 የአገሪቱን ጤና ሚኒስቴር ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው ሰራተኞች አስከ መስከረም 15 ድረስ ቢያንስ አንዴ ክትባቱን እንዲወስዱ ያን ካልሆነ ግን ስራቸውን እንደሚያጡ ከአንድ ወር በፊት ተናግረው ነበር።
በደቡባዊ ፈረንሳይ በምትገኘው ኒስ ከተማ ከሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች መካከል 450ዎቹ ክትባቱን ባለመውሰዳቸው ከስራ መታገዳቸውን ተከትሎ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።
የጣና ባለሙያዎች ከስራ መታገዳቸውን ተከትሎ በከተሞች ከአስቸኳይ ህክምናዎች ውጪ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች በመቋረጥ ላይ መሆናቸውን ዘገባው አክሏል።