ፖለቲካ
ዚምባቡዌ የኮቪድ 19 ክትባት የማይከተቡ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን ሊያጡ ይችላሉ አለች
የዚምባቡዌ መንግስት በሌላ በኩል ማንንም ሰው ክትባት ውሰዱ ብሎ አላስገድድም ሲልም ይደመጣል
የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው ተግባሩ ህገ መንግስቱን የጣሰ ነው ሲሉ ተቃውሞዋቸውን አስምተዋል
ዚምባቡዌ የኮቪድ 19 ክትባት ያልተከተቡ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ አስጠነቀቀች።
የሀገሪቱ የፍትህ ሚኒስትር ዚያምቢ ዚያምቢ፤ መንግስት ማንንም ሰው ክትባት ውሰዱ ብሎ አያስገድድም፤ ሆኖም ግን ክትባቱን የማይወሰዱ የመንግስትሰራተኞች ስራውን ሊያጡ ይችላሉ ብለዋል።
ለመንግስት መስራት የሚፈልግ ሰው የተቀመጡ ህጎችን ማከበር የግድ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ የሀገሪቱ መንግስት የቀጠራችሁ ከሆነ መከተብ የግድ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የህግ ባለሙያዎች በበኩላቸው ሰራተኞቸን የሚያስገድድ የህግ መሰረት የለም፤ ጉዳዩ ህገ መንግስቱን የጣሰ ነው ሲሉ ተቃውሞዋቸውን አስምተዋል።
የፍትህ ሚኒስትሩ ዚያምቢ በበኩላቸው መንግስት ህጎችን እንዲያወጣ እና እንድያሻሽል በህገ መንግስቱ የተቀመጠ ክልከላ የለም ብለዋል።
በዚምባቡዌ እስካሁን በ126 ሺህ 163 ሰዎች ላይ ኮቪድ 19 የተገኘ ሲሆን፤ 4 ሺህ 532 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን አጥተዋል።
እንደ ሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ሪፖርት እስካሁን 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዜጎች የመጀመሪያውን ዙር ክትባ የወሰዱ ሲሆን፤ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተከትበዋል።