ዩኤኢ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት የተከተቡ ጎብኚዎች ወደ አገሬ መግባት ይችላሉ አለች
አገሪቱ ከነገ ከሰኞ ጀምሮ ክትባት የወሰዱ የተለያ ሀገራት ዜጎች መግባት እንደሚችሉ ገልጻለች
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘመው የ2020 ዱባይ ኤክስፖ ከአንድ ወር በኋላ ይከፈታል
ዩኤኢ የኮሮና ቫይረስ የተከተቡ ጎብኚዎች ወደ አገሬ መግባት ይችላሉ አለች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከዚህ በፊት የኮሮና ቫይረስ መስፋፋቱን ተከትሎ የጉዞ እገዳ ጥላ ነበር።
አገሪቱ ከዚህ ውስኔ ላይ የደረሰቸው በአገር አቀፍ ደረጃ በየዕለቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር ከአንድ ሺህ በታች በመሆኑ ነው።
ህይወት ከኮቪድ በፊት የነበረው አይነት በመመለስ ላይ በመሆኑ የኮሮና ቫይረስ ከትባት የወሰዱ ዜጎች ወደ አገሬ መግባት ይችላሉ ብላለች።
ውስኔው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘመው የ2020 ዱባይ ኤክስፖ ለመከፈት አንድ ወር ሲቀረው መደረጉ በንግድ ትርኢቱ ለሚሳተፉ እንግዶች ጥሩ አጋጣሚ ነው ተብሏል።
ወደ ዩኤኢ የሚመጡ ጎብኚዎች በዓለም ጤና ድርጅት እውቅና የተሰጣቸውን ክትባቶች ከተከተቡ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ዜጎች ወደ አገሪቱ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።
ይሁንና ጎብኚዎቹ ከትባት መውሰዳቸው እንዳለ ሆኖ በአውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ተጨማሪ መርመራ ይደረጋልም ተብሏል።
የዱባይ ዓለም አቀፍ 2020 የንግድ ትርዒት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለአንድ ዓመት ተራዝሞ የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።
በዩኤኢ ከ715 ሺህ በላይ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሲሆን ከ2 ሺህ በላይ ደግሞ ህይወታቸውን አጥተዋል።