ፈረንሳይና ለ6ኛ ጊዜ የቤላሩስ ፐሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አሌክሳነደር ሉካሼንኮ ዕውቅና አልሰጠችም
በቤላሩስ መንግሰት፤ ከሀገር የተባረሩት የፈረንሳይ አምባሳደር ኒኮላስ ዲ ሎከስት፤ ሚኒስክን ለቀው መውጣታቸው ተነግሯል።
እስከ ዛሬ ሰኞ ድረስ ቤላሩስን ለቀው እንዲወጡ ታዘው የነበሩት አምባሳደሩ በትናትናው ዕለት ሀገሪቱን ለቀው መውጣታቸውን በቤላሩስ የፈረንሳይ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ለኤ.ኤፍ.ፒ አስታውቀዋል።
የ57 ዓመቱ አምባሳደር ኒኮላስ ዲ ሎከስት ባሳለፍነው ዓመት ነበር ፈረንሳይን በመወከል ወደ ሚኒስክ የተመደቡት።
እንደ ቤላሩስ ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ አምባሳደር ኒኮላስ ዲ ሎከስት ከሀገር እንዲወጡ የተደረጉት ለፕሬዝዳንት አሌክሳነደር ሉካሼንኮ የሹመት ደብዳቤያቸውን ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው።
አምባሳደር ኒኮላስ ዲ ሎከስት ከቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቨላድሚር ማኪ ጋር ባሳለፍነው ዓመት ህዳር ወር ላይ ተገናኝተው እንደነበረ ተነግሯል።
በወቅቱም የቤላሩሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደሩ ከጥቅምት 8 በፊት ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ አሳውቀዋቸው እንደበረ የፈረንሳይ ኤምባሲ አስታውቋል።
ፈረንሰይ ልክ እንደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ለ6ኛ ጊዜ የቤላሩስ ፐሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ምርጫ አጭበርብረዋል በሚል ዕውቅና አልሰጠችም።
የአውሮፓ ህብረትም በተደጋጋሚ በነሃሴ ወር በሀገሪቱ የተካሄደው ምርጫ “ነጻ እና ፍትሃዊ” አልነበረም በማለት በፕሬዝዳንት አሌክሳነደር ሉካሼንኮ ላይ ማእቀብ ጥሏል።