አዲሱ ጭግት የተቀሰቀሰው ፕሬዝዳንት እድሪስ ዴቢ በተገደሉበት ቦታ መሆኑ የሽግግር መንግስቱ አስታውቋል
በምእራባዊ ቻድ ፕሬዚዳንት እድሪስ ዴቢ ባለፈው ሳምንት በተገደሉበት ቦታ በመንግስት ወታደሮችና በአማፂያን መካከል አዲስ ግጭት መቀስቀሱን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
የእድሪስ ዴቢን ሞት ተከትሎ ስልጣን የያዘው ወታደራዊ መንግስት ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ውጊያው በካኔም መቀጠሉንና፣አሁንም ውጊያው እንደሚቀጥልና ካልሆነ አለመረጋት እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡
የወታደራዊ ምክርቤቱ በ37 አመቱ በዴቢ ልጂ ማሃመት እድሪስ ዴቢ መመራት ላይ ይገናል፡፡ ውጊያው በበረሃማው ካኔም ግዛት እየተካሄደ ሲሆን ይህ ቦታ ከቻድና ዋና ከተማ ኒጃሚና 180 ኪሊሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡
አማጺያኑ በዋናነት ጎራን ከሚባሉ የጎሳ አባላት የተውጣጡ ሲሆን የአማጺ ቡድኑ ስም ፍሮንት ፎር ቸንጅና ኮንኮርድ ይሰኛል፡፡ ሮይተርስ ምንጮችን ሰቅሶ የቻድ ጦር መመታቱን ዘግቧል፡፡ ዴቢ የሞቱት መቀመጫቸውን ሊቢያ ካደረጉ አማጺያን ጋር በነበረው ዉዲያ ቆስለው ነበር ህይወታቸው ያለፈው፡፡
የቻድ አማጺያን በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ዋና ከተማዋ ኒጃሚና ከትናንት ጀምሮ በመቅረብ ላይ እንደነበሩ የሚገልጹ መረጃዎች ወጥተው ነበር፡፡
የሀገሪቱ መንግስት እና ፓርላማ እንዲበተን የወሰነው የሀገሪቱ ጦር የሽግግር ምክር ቤት አቋቁሟል፡፡ ቀጣይ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ የሀገሪቱ ጦር ለ18 ወራት የሚቆየውን የሽግግር ጊዜ እንዲመራም ተወስኗል፡፡