በቀጣዮቹ ዓመታት እጅግ ተፈላጊ የሚሆኑ የሙያ መስኮች የትኞቹ ናቸው?
ኮሮና ቫይረስ የዓለማችንን የስራ ባህል እንዲቀየር ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ሆኗል
የተወሰኑ የስራ መስኮች በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክንያት ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ ይገኛል
በቀጣዮቹ ዓመታት እጅግ ተፈላጊ የሚሆኑ የሙያ መስኮች የትኞቹ ናቸው?
ከሰው ልጆች ፍላጎት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ስራ በየጊዜው እንደ ዘመኑ ይቀያየራል።
ከአራት ዓመት በፊት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንደተከሰተ አካላዊ ንኪኪን ለማስቀረት በሚል በርካታ ተቋማት ስራዎቻቸውን ወደ ቢሮ ሳይመጡ መከወን ችለው ነበር።
ይህ አሰራር የጊዜ ብክነት እና ወጪ መቀነሱን ተከትሎ አሁንም ድረስ ስራዎችን ከመኖሪያ ቤት ሆነው መስራትን የሚከተሉ አሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ቴክኖሎጂዎች ስራዎችን በማቅለላቸው በየጊዜው አዳዲስ የስራ ዘርፎች ከመፈጠራቸው ባለፈ ከዚህ በፊት የነበሩ ሙያዎች እንዲጠፉ አልያም ተፈላጊነታቸው እንዲቀንስ ሆኗል።
የአውስትራሊያው ቪክቶሪያ ዩንቨርስቲ በቀጣዮቹ ዓመታት እጅግ ተፈላጊ ያላቸው የሙያ መስኮች ይፋ አድርጓል።
እንደ ተቋሙ ጥናት ከሆነ ጤና፣ የግንባታ ሙያዎች፣ ትምህርት እና ስልጠና ፣ ሳይበር ሴኩሪቱ እጅግ ከሚፈለጉ የሙያ መስኮች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።