"ጂቢዩ-57" የተሰኘው ቦንብ፣ አማሪካ የኢራንን የኑክሌር መሳሪያዎች እመታለሁ እያለች የምታስፈራራበት ቦንብ ነው
""ጂቢዩ-57" አማሪካ የኢራንን የኑክሌር መሳሪያዎች እመታለሁ እያለች የምታስፈራራበት ቦንብ ነው።
ይህ የአሜሪካ ቦንብ ምስል ይፋ ከሆነ በኋላ እውን አሜሪካ የኢራንን የኑክሌር መሳሪያ ማምረቻ ማዕከላትን ትመታ ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
የአሜሪካ ጦር የዚህን ቦንብ ምስል ይፋ አድርጓል።
በኑክሌር ኘሮግራሞ ምክንያት የአሜሪካ እና ኢራን ግንኙነት በጦዘበት ወቅት ይፋ የተደረገው ይህ ከመሬት በጥልቀት በመግባት ከመሬት ውስጥ ያሉ የኑክሌር መሳሪያ ማከማቻዎችን ሊመታ የሚችል ነው ተብሏል።
የአሜሪካ አየር ኃይል የ"ጂቢዩ -57" ፎቶዎች ፖስት ከደሰገ በኋላ ማጥፋቱን ገልጿል። አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው አየር ኃይሉ ፎቱን ያጠፋው ምናልባት ሚስጢራዊ ዝርዝሮችን ይዟል በሚል ሳይሆን እንደማይቀር ገልጿል።
የቦንቡ ፎቱ ይፋ የሆነው ኢራን ይህ የአሜሪካ ቦንብ መድረስ የማይችልበት የኑክሌር ማበልጸጊያ ቦታ ስርታለች የሚል ዘገባ መውጣቱን ተከትሎ ነው።
ኢራን እና አሜሪካ በኑክሌር ጦር መሳሪያ ጉዳይ አለመግባባት ውስጥ ከገቡ ቆይተዋል።