ፖለቲካ
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የውሃ ስር የኑክሌር ድሮን ሙከራ አደረገች
ፒዮንግያንግ የውሃ ስር ድሮን ሙከራ ስታደርግ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው
ሄሊ 2 የተበለው የኑክሌር ድሮን 1 ሺህ ኪ.ሜ ተጉዟል
ሰሜን ኮሪያ ሁለተኛውን የውሃ ስር የኑክሌር ተሸካሚ ድሮን ሙከራ ማድጓን አስታውቃለች።
ሄሊ 2 በኮሪያ ቋንቋ ሱናሚ የሚል መጠሪያ ያለው ድሮን ሙከራ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሹለተኛ ጊዜ የተካሄደ መሆኑም ነው የተነገረው።
በባህር ስር የመለንቀሳቀሱ የጠላት ኢላምን ለማጥቃት ታስበው የተሰሩህ ጀውሃ ስር የኑክሌር ተሸካሚዎቹ በሰዓት 1 ሺህ ኪሎ ሜትር መጓዛቸውም ተነግሯል።
ሰሜን ኮሪያ ከሳምንት በፊት ሄሊ 1 ስትል የሰየመችውን የውሃ ስር ድሮን ላይ ሙከራ አድርጋ እንደነበረ ይታወሳል።
ድሮኑ ከውሃ በታች ለ59 ሰአታት ያለማቋረጥ መንቀሳቀሱንና ይህም የአሜሪካን እና የደቡብ ኮሪያን ታጣቂ ሃይሎችን ለማስፈራራት የተደረገ ልምምድ ነው ተብሏል።
በፒዮንግያንግ የተሞከረችው የኑክሌር አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ድሮኑ “ራዲዮአክቲቭ ሱናሚ” ማስነሳት ይችላል።