ዋና ጸሐፊው ወደ ሲሁል ያቀኑት ለፒዮንግያንግ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ተብሏል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ሰሜን ኮሪያ ኑክሌር እንዳታበለጽግ እና ያበለጸገችውንም እንዳትጠቀም ለማስደረግ ቁርጠኛ መሆኑን መሆኑን አስታወቀ፡፡
ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ከደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ጋር በተገናኙበት ወቅት ሰሜን ኮሪያ ኑውክለር ማበልጸጓን እንድታቆም ለሚደረግ ጥረት ተቋማቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
ተመድ፤ ፒዮንግያግ የታጠቀችውን ኑውክለር እንዳይኖራት ለማድረግም ሙሉ ቁርጠኝነት እንዳለው ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡
ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ዛሬ በሲሁል ከተማ ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ሁለቱ ወገኖች፤ በኮሪያ ፔንሱላ ዙሪያ፤ የጦር መሳሪያ ምርትን መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋው ተሰምቷል፡፡
ደቡብ ኮሪያ በሀገራት መካከል ሰላም እንዲኖር ቁርጠኛ መሆኗንም ዋና ጸሐፊው መስክረዋል፡፡ አንቶኒ ጉቴሬዝ፤ ሰሜን ኮሪያ ኒውክለር እንዳይኖራትና ያላትንም ለማስፈታት ተመድ ቁርጠኛ መሆኑን በአጽንኦት መናገራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ያበለጸገችውን ኒውክለር እንድተውና በቀጣይም እንዳይኖራት ለማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግልጽና የተብራራ አቋም አለው ብለዋል ዋና ጸሐፊው፡፡ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ሰሜን ኮሪያን የጠሩት ሀገሪቱ ራሷን በምትጠራበት “ዴሞክራቲክ ፒፕልስ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮሪያ” ብለው ነው፡፡
የተመድ ዋና ጸሐፊ በኮሪያ ቀጠና ሰላም፣ መረጋጋትና ጸጥታን ለማረጋገጥ የሰሜን ኮሪያን የኑውክለር ትጥቅ እንዳይኖራት ማድረግ ግደታ መሆኑን መናገራቸው ተገልጿል፡፡ ይህንኑ ጉዳይም ለደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ነግረዋቸዋል ተብሏል፡፡
ደቡብ ኮሪያ ለዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በምታደርገው አስተዋጽኦ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ላሳየችው ጥረት ዋና ጸሐፊው እንዳመሰገኗት ተገልጿል፡፡ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ደቡብ ኮሪያ የገቡት ትናንት ምሽት ሲሆን ወደ ስፍራው ያቀኑትም የሰሜን ኮሪያን የኒውክለር መሳሪያ ዓለም እንደማይታገሰው መልዕክት ለማስተላለፍ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡