የህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል የማስቀመጥ ሥራ ተከናወነ
የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካሉ በዩኒት 10 ላይ ሀይል ማመንጫ ላይ ነው የተቀመጠው
የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ነው
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የጀነሬተር አንቀሳቃሽ አካል( Rotor) የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት መከናወኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታወቀ።
በቅርቡ ኃይል እንደሚያመነጭ ከሚጠበቁት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለት ዩኒቶች መካከል በዩኒት 10 ላይ የተርባይን ጀነሬተር ተሽከርካሪ አካል (Rotor) በቦታው ላይ የማስቀመጥ ሥራ ዛሬ በስኬት ተከናውኗል።
ሮታሩና አብረው ያሉት አካላት 840 ቶን ክብደት ያላቸው ሲሆን ሮተሩ ብቻውን 780 ቶን ይመዝናል።
ሮተሩ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው ጫፍ ድረስ ያለው አጋማሽ ርዝመት ወይም ዳያሜትር 11 ነጥብ 7 ሜትር መሆኑንም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አስታውቋል።
- ግድብ አሁን ባለው የግንባታ ቁመት 400 ሜጋ ዋት ኃይል ያመነጫል-የግድቡ ተደራረዳሪ
- ከ2 ወር በኋላ ኃይል ማመንጨት ለሚጀምረው የህዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ መስመር ፍተሻ ተጀመረ
የሮተሩና የተርባይን አካላቶች በአግባቡ መገጠም የኃይል ማመንጨት የሙከራ ስራ ለመጀመር መቃረቡ አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ብሏል።
የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሳለፍነው ሐምሌ 12 ቀን 2013 ዓም ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌቱ መጠናቀቁ ይታወሳል።
“ሁለተኛው ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቁም 2 ተርባይኖችን ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገውን የውሃ መጠንና ይዘናል ማለት ነው” ሲሉም የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢ/ር ስለሺ በቀለ በወቅቱ መግለጻቸው ይታወሳል።