የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት ዕቅድና ጊዜ መሰረት እየተካሄደ ነው- ዶ/ር ኢ/ር ሲለሺ
የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቦርድ አባላትና ኢትዮጵያ እልክትሪክ ኃይል አመራሮች የግድቡን የግንበታ ሂደት ጎብኝተዋል
የህዳሴ ግድብ የግንባታ ሂደት ከ80 በመቶ በላይ ተጠናቋል
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በተያዘለት እቅድን መሰረት እየተካናወነ መሆኑን የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ አሰታወቁ።
ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ባወጡት መረጃ በትናትናው እለት የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ቦርድ አባላት ከኢትዮጵያ እሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን የግድቡን የግንበታ ሂደት መጎብኘታቸውን አስታውቀዋል።
በጉብኝቱም የታላቁ የህዳሴ ግድብ የግንብታ ሂደት በተያዘለት እቅድ እና ጊዜ መሰረት እየተከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን አስታውቀዋል።
ግድቡ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲከናወን በግንባታው ሂደት ላይ በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች፣ የግንባታ አማካሪዎች እና በግድቡ ዙሪያ ድጋፍ ለሚያደርጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከ80 በመቶ በላይ ግንባታው የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በያዝነው የክረምት ወራት 18 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ መያዝ እንደሚጀምር ይጠበቃል።
በነሀሴ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ቀናት ሁለት ተርባይኖች 700 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት አንደሚጀምሩ የውሃ፤መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከዚህ በፊት መናገራቸው ይታወሳል።
የፊታችን ነሀሴ ወር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫት እንደሚጀምሩ መገለጹ ይታወሳል።
ተርባይኖቹ እያንዳንዳቸው 350 ዋጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፤ በድምሩ በቅድመ ኃይል ማመንጨት ሥራው 700 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያመነጩ ይሆናል።