በጀርመን ለ142 ዓመታት ያልተከሰተ የአየር ንብረት ክስተት
መስከረም 2023 በሀገሪቱ በጣም ሞቃታማው ወር መሆኑ አሳይቷል
በሀገሪቱ አማካኝ የሙቀት መጠኑ 17.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል
የጀርመን የሜትሮሎጂ አገልግሎት ይፋ ያደረገው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት በጎርጎሮሳዊያኑ 1881 የሙቀት መጠን መለካት ከተጀመረ ወዲህ፤ መስከረም 2023 በሀገሪቱ በጣም ሞቃታማው ወር መሆኑ አሳይቷል።
አገልግሎቱ እንዳስታወቀው በመስከረም የታየው የሙቀት መጠን ከዚህ በፊት ታይቶ ወደ ማይታወቅ ደረጃ ከፍ ብሏል።
- ከባድ ሙቀትና ወበቅ በሰው ልጆች ላይ ምን አይነት የጤና እክል እያደረሰ ነው?
- እሳተ ገሞራ ለከባቢ አየር ሙቀት መጨመር ዋና ምክንያት ነው የሚባለው ምንያህል እውነት ነው?
የጀርመን አማካኝ የሙቀት መጠኑ 17.2 ዲግሪ ሴልሺየስ ደርሷል።
ይህም ማለት በመስከረም ወር የታየው የሙቀት መጠን ከጎርጎሮሳዊያኑ 1961 እስከ 1990 ከነበረው ዓለም አቀፍ የሙቀት የማጣቀሻ በ3.9 ዲግሪ ከፍ ያለ ነው።
በአሁኑ ወቅት ማጣቀሻ ከሆነው ከ1991 እስከ 2020 ካለው ሙቀት በ3.4 ዲግሪ ሞቃታማ ነው።
መስከረም 2023 የአየር ከባቢ ሁኔታ መመዝገብ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለተኛው ጸሀይአማ ወር ነበር ተብሏል።
የጀርመን የሜትሮዎሎጂ አገልግሎት እንደገለጸው የሁለቱም ወቅቶች የአየር ሁኔታ በጣም ደረቅ ነው።
አገልግሎቱ በመስከረም ወር የተመዘገበው ክብረ-ወሰን የሆነ ከፍተኛ ሙቀት በአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ መሆናችንን የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው ብሏል።