እስከ 40ዲግሪ ሴልሺየስ የሚደርሰው የሙቀት መጠን እድሜያቸው 75 እና ከዚያ ባሉ ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አስከትሏል
የጣሊያን የጤና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በጣሊያን ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተከሰተ በኋላ በሐምሌ ወር የተመዘገው የሞት መጠን ከመጀበኛም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው።
የሞት ምጥነት ከመደበኛው ሰባት በመቶ ከፍ ብሏል።
በጣሊያን በሳርዲና እና በሄልስቶን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራኞች በርብርብ ላይ መሆናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ባለፈው ወር ደቡብ አውሮፖ በከፍተኛ የሙቀት መጠን ከተመታ በኋላ ጣሊያን ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጥሮባታል፤ ሙቀቱ የአሳት አደጋ እና የሞት መጠን እንዲጨምር አድርጓል።
የጣሊያን የጤና ሚኒስቴር በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ የተከሰተው ከባድ ሙቀት በሐምሌ ወር የተመዘገበው የሞት መጠን በፈረንጆቹ 2015 እስከ 2019 በተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገው የሞት መጠን እንዲጨምር አድርጎታል ተብሏል።
እስከ 40ዲግሪ ሴልሺየስ የሚደርሰው የሙቀት መጠን እድሜያቸው 75 እና ከዚያ ባሉ ሰዎች ላይ የሞት አደጋ አስከትሏል።
የሞት መጠን መጨመሩ እንደ ባሪ፣ ካታኒያ እና ሬጊዮ ካላብሪያ ባሉት የጣሊያን ከተሞች ላይ በግልጽ ይታያል። ከዚህ በተቃራኒው በሰሜን ጣሊያን የሙቀት መጠን ዝቅተኛ በሆነባቸው ቦታዎች የሞት መጠኑ ከተገመተው በታች ዝቅ ያለ ነው ተብሏል።