እሳተ ገሞራ ለከባቢ አየር ሙቀት መጨመር ዋና ምክንያት ነው የሚባለው ምንያህል እውነት ነው?
ለአየር ብክለት የሰው ልጅ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ
ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሰው ልጅ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው የካርበን ዳይ ኦክሳይድ መጠን እሳተ ገሞራ ከሚያመነጨው 100 እጥፍ ይበልጣል
እውን እሳተ ገሞራ አሁን በዓለም እያየነው ላለው የሙቀት መጠን መጨመር ዋና ምክንያት ነውን፤ ወይስ በሰው ልጅ የተፈጠረ አሉባልታ ነው?
የአየር ብክለት ለውጥ የሚያመጣውን ችግር ለመቀነስ የማይንቀሳቀስ ሰው ለድክመቱ ምክንያት ይፈልጋል። የሰው ልጅ እሳተ ገሞራ የሚለቀውን የግሪን ሀውስ ጋዝ ልቀትን ለሙቀት መጨመር ምክንያት ያደርጋል።
ነገርግን እውን ጋዞቹ የሚለቀቁት በእሳተ ገሞራ ነው?፤ እና ይህስ ለአየርንብረት ለውጥ ዋነኛ ምክንያት ነው?
እሳተ ገሞራ
እሳተ ገሞራ ሁልጊዜ የሚለቀው ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ጋዝ ወደ ከባቢ አየር ይለቀቃሉ። በእሳተ ገሞራ ጊዜ ድንጋዮች እና የቀለጠው ነገሮች የካርበን ዳይኦክሳይድ ምንጮች ናቸው።
እሳተ ገሞራ በሚከሰት ጊዜ ከካርበንዳይኦክሳይድ በተጨማሪ ሰልፈሪክ አሲድንም ይለቃል።
ሳይንቲስቶች እንዳረጋገጡት ከሆነ የአየርንብረት ለውጥ ዋነኛ መንስዔው የተወሰኑ ሰዎች እንደሚሉት እሳተ ገሞራ ሳይሆን የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ነው።
ለአየር ብክለት የሰው ልጅ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ መሆኑን ሳይንቲስቶች ይናገራሉ። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የሰው ልጅ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀው የካርበን ዳይ ኦክሳይድ መጠን እሳተ ገሞራ ከሚያመነጨው 100 እጥፍ ይበልጣል።
እንደሳይንቲስቶቹ ገለጻ እሳተ ገሞራ የጸሀይ ነጸብራቅ እንዲመለስ በማድረግ ሙቀት እንዲቀንስ እና የዓለም አየር ንብረት እንዲቀዘቅዝ ይረዳል። በእኛ ባለንበት አለም እሳተ ገሞራ የዓለም የአየር ንብረት ሙቀት መጨመር ላይ ግንባር ቀደም ሚና የለውም። ነገርግን የሰው ልጅ ለሙቀት መጨመር የተለያየ ሰበብ ቢፈልግም ለሙቀት መጨመር ዋነኛ አስተዋጽኦ ያለው እሱ ነው ይላሉ ሳይንቲስቶች።